top of page

ነሃሴ 18/2015 በሰሜን ሸዋ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ /መኮይ/ ገና በጠዋቱ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


ገና ሳይነጋ ንጹሃንን ሊፈጅ ወደ በአንጾኪያ አካባቢ ጦርነት ቢከፍትም ከህዝባዊ ሃይሉ ጥይት ግን ሊያመልጥ አልቻለም ብለዋል ምንጮቹ።


ህዝባዊ ሃይሉ የገዳዩን ስብስብ ሙትና ቁስለኛ አድርጎ የተረፈውም እግሬ አውጪኝ ሲል ላይ ፊልም እንጂ በእውን የሚታይ ክስተት አይመስልም ብለዋል ሁኔታው ሲገልጹት።


መሳሪያውን በገፍ እያስረከበ ያለውና አሁንም ለመግደል ሳይሆን ለመሞት የሚመጣው የገዳዩ ስብስብ አሁንም የተረፈውን ሃይል ከየቦታው ለቃቅሞ መመለሱን ተናግረዋል።


ይሄ ተለቃቅሞ የተመለሰ ሃይል ደግሞ በዚህ ሰአት ህዝባዊ ሃይሉን መንካት እንደማይችል አውቆ ንጹሃን ላይ ጥይት ማዝነብ መጀመሩን ተናግረዋል።


እስካሁንም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገለዋል ቁስለኛ ሆነዋል ብለዋል ምንጮቹ።


በምስራቅ ጎጃም ደግሞ ህዝባዊ ሃይሉ ዳግም ታሪክ መስራቱን ሳይጠቁሙ አላለፉም።

ትላንት ይላሉ ምንጮቹ በዞኑ አዋበል ወረዳ የጎደና ቀበሌ ላይ በገዳዩ ስርአት ሃይል ላይ በወሰደው እርምጃ ትጥቁን ብቻ ሳይሆን በ 6km ክልል ውስጥ የሬዲዮ ግንኙነት ማድረግ የሚያስችለውን ሙሉ ወታደራዊ የሬዲዮ መገናኛን በቁጥጥር ስር ማድረጉን ተናግረዋል።


ህዝባዊ ሃይሉ ከነፍስ ወከፍና ከግል መሳሪያ ውጪ እንዲህ አይነት የመገናኛ መሳሪያ በቁጥጥር ስር ሲያውል ለመጀመራያ ጊዜ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ትላንት ደግሞ ይላሉ የኢትዮ 360 ምንጮች በሰሜን ጎጃም ዞን በአንዳንድ ከተሞች እንቅስቃሴ ቆሞ መዋሉን አመልክተዋል።


የመራአዊና የዳንግላ አካባቢዎችን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎችን ያካተተው ይሄው አካባቢውን ጸጥ የማድረጉ ዘመቻ በመቆሙ ተነገረ በአማራ ክልል በሰሜን ጎጃም ዞን በአንዳንድ ከተሞች በዛሬው ዕለት በባህርዳርም መቀጠሉን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በባህርዳር ዛሬ ማለዳ ላይ ከትራንስፖርት ውጪ ቆሞ የነበረው የማህብረሰቡ እንቅስቃሴ ከሰአት በኋላ ወደ ቦታው መመልሱንም ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በክልሉ ነጹሃንን ለመፍጀት በትጥቅ አስፈታለሁ ሰበብ የገባው የሰው በላው ሃይል እየደረሰበት ያለው ውርደት ቤተመንግስቱን በከባድ ፍርሃት እንዲርድ እያደረገው ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

ነሐሴ 18/2015 የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ገለጹ።

በደቡብ ክልል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ክልል ውስጥ ያሉው የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ። አዲስ ተቋቋመ በተባለውና ከፍተኛ ቁጥር...

ነሐሴ 18/2015 የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች በአዲስ መልክ ተደራጅተው መነሳታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

የአማራ ክልልን ወደሌላ ብጥብጥና ቀጠና ለማምራት የተነሱ የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች በአዲስ መልክ ተደራጅተው መነሳታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ። እነዚህ ቡድኖች የብአዴንን ሽንፈት አምነው መቀበል...

Comments


bottom of page