top of page

ነሐሴ 10/2015 የግርማ የሺጥላ ተከታይ የነበረ ስብስብ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ነኝ በሚል ወጣቶችን እያታለለ ነው

ነሐሴ 10/2015

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ወረዳ መሀልሜዳ ከተማ አስተዳደር የሟሹ የግርማ የሺጥላ ተከታይ የነበረ ስብስብ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ነኝ በሚል አጀንዳ ወጣቶችን እያታለለ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

ይሄንን ስብስብ እየመራ ያለው ደግሞ አበባው ቤልጂግ የተባለ የግርማ የሺጥላ የአክስት ልጅ ነው ሲሉም ያጋልጣሉ።


` ይሄው ግለሰብ ዛሬ የፋኖ መሪ በመምሰል ወጣቶችን በመመልመል ትጥቅ ከመሐልሜዳ ከተማ አስተዳደር ሚንሻ ጽህፈት ቤት ከተቀበለ በኋላ ለፋኖነት የገቡ ልጆችን በፋኖ ስም የብልፅግና ታጣቂና ጠባቂ እያደረጋቸው ነው ብለዋል ምንጮቹ።


አበባው ቤልጅግ የተባለ ይሄው ግለሰብ የቫት ተመዝጋቢ የጅምላ አከፋፋይ ነጋዴም ሲሆን ቀደም ሲል እራሱን የፋኖ መሪ በማድረግና ሌላ አጅንዳ በመያዝ ፋኖ እንዳይደራጅ ሴራ ሲሰራና ሲያደናቅፍ መቆየቱንም ሳይናገሩ አላለፉም።


ለዚህም ውለታው በአገዛዙ በኩል የገንዘብ መዝረፊያ መንገድ ተመቻችቶለታል ብለዋል ምንጮቹ።

ትክክለኛው የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ወደበርሃ ወርዶ እራሱን እያደራጀ በነበረበት ወቅት ይሄ ግለሰብ ግን ፋኖዎችን በትኖ የስራ አጥ ወጣቶችን ስራ በመንጠቅ በወረዳው አስተዳዳሪ በሀይሌ የሺጥላ የእዝ ደብዳቤ ትዕዛዝ የማዕድን ሽያጭ ዘረፋ ላይ ተሰማርቶ ቆይቷል።


እናም ይላሉ አበባው ቤልጅግ የተባለው ሰው በጥቅም እራሱን አሳውሮ የአገዛዙን ተልእኮ እየፈፀመ ስለሆነ ህዝባዊ ሀይሉ ባለው አደረጃጀት የፋኖ መሪ በመቀየር አደረጃጀቱን ከሰርጎገብ መከላከል የገባዋል ሲሉም ጥቆማቸውን አስቀምጠዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የደብረ ብርሃን ከንቲባ ከሰው በላው ስብስብ ጋር በመሆን በከተማዋ ያሉ ባለሃብቶችንና ወጣቶችን በማሳፈን ላይ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page