ነሐሴ 11/2015
በባህርዳር ከተማ በስድስቱም ክፍለ ከተሞች ባሉ የብልጽግናው ጽህፈት ቤቶች ላይ ትላንት ምሽት ጥቃት መፈጸመኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ምሽት አንድ ሰአት ላይ በስድስቱም ጽህፈት ቤቶች ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ ምን ይህል ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን አለመታወቁንም አመልክተዋል።
በስድስቱም ጽህፈት ቤቶች በተመሳሳይ ሰአት የተፈጸመው ጥቃት የተወሰደው ደግሞ ባልታወቁ ሰዎች መሆኑንም ምንጮቹ አንስተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በባህርዳና ዙሪያው የሚቀሳቀሰው ህዝባዊ ሃይሉ በተደጋጋሚ በገዳዩ ቡድንም ሆነ በሆድ አደሩ የብአዴን ሚሊሻና አድማ ብተና ላይ ከፍተኛ ቁጠ ያለው መሳሪያን መማረኩን ይናገራሉ።
በቅርቡ ሁለት ፓትሮል የአድማ ብተና ሃይል ጥቃት ሊፈጽም ወደነሱ ቢላክም እነሱ ግን ይዞት የመጣውን 36 መሳሪያና አንድ መትረየስ ከነሃይሉ መማረኩንም ይናገራሉ።
ከዛም ሌላ ከ100 በላይ ክላሾችን በቀላሉ የማረከው ይሄው የህዝባዊ ሃይሉ ቡድን የማረካቸውን የአድማ ብተና አባላት ስልጠና ሰተው በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም አመልክተዋል።
ከፌደራል የመጣው ጢስ አባይ ላይ ሊገላቸው የመጣውን የገዳዩን ስርአት ሙሉ በሙሉ ሲደመስስ 18ቱ ደግሞ በገዛ ፈቃዳቸው እጃቸውን እንደሰጡ ይናገራሉ።
የክልሉ ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ቀኝ እጅ የሚባለውን ዋና ኢንስፔክተር ሙቀት የሚባለውን የማረከው ህዝባዊ ሃይል የ10ኛ ፖሊስ ጣቢያን ተቆጣጥሬያለሁ ብሎ ያስብ የነበረው ሃይልም ወገኔን አልወጋም በሚል ከነሱ ጋር እንዲቀላቀል ማድረጉን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የሚናገሩት።
አሁንም ከተማ ላይ በገዳዩ ስርአት በንጹሃን ላይ የተጀመረውን ግድያ ለማስቆም ከከተማው ይራቅ እንጂ ተልእኮውን ግን በአግባቡ እየፈጸመ ነው ሲሉ ምንጮቹ አመልክተዋል።