top of page

ነሐሴ 11/2015 በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች የአማራ አመራሮች፣ባለሃብቶችና ወጣቶች በገፍ እየታሰሩ ነው!

ነሐሴ 10/2015

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች የአማራ ተወላጅ የሆኑ አመራሮች፣ባለሃብቶችና ወጣቶች በገፍ እየታሰሩ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


አካባቢው ላይ የአማራ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ጨለማን ተገን በማድረግ ማፈንና ማሳደዱ አይን ባወጣ መልኩ ቀጥሏል ብለዋል።


የሚገርመው አፈናው ብቻ አይደለም ድብደባም ጭምር የሚፈጽመው ይሄው አፋኝ ቡድን ሌሊት ስዓት እላፊ በቤት ጣሪያ እና በአጥር ላይ እየገባና የቤት በሮችን በመገንጠል ጭምር የሚፈጽሙት አፈና ነው ብለውታል።


እስካሁንም በዚህ አፈና የከተማው ንግድ ኢንዱስትሪ ባለሞያና የምክርቤት አባል ሳሙኤል ዘውዱ፣ ጠበቃና የህግ አማካሪው  መታገስ አያሌው፣ አበበ አየለ፣ አበባው አሽኔ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ም/አስደተዳደሪና የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ ዘመተ አይፎክሩ፣  አስደግድግ አሰማኸኝ የሀገር ሽማግሌ ከነ ልጁና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል።


አሁንም በየአቅጣጫው ያለው አፈና አይን ባወጣ መልኩ ቀጥሏል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page