ነሐሴ 11/2015
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የሚገኘውን የሸማቾች ኅብረት ሱቅ ያለበትን ቦታ ለአንድ ፓስተር ባለቤት ለመስጠት ነባሩ ተገልጋይ ቦታውን ልቀቅ መባሉን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ከሶስት ወር በፊት የህዝብ መገልገያ የነበረውን ሻላ መናፈሻን ለአንድ ተረኛ ግለሰብ የሰጠው አካል አሁን ደግሞ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበሩን ሱቅ ያለበትን ቦታ ደግሞ ለአንዷ የፓስተር ባለቤት ለመስጠት ተገልጋዩ ማህበረሰብ ቦታውን ልቀቅ ተብሏል ይላሉ።
የሸማቾች ኅብረት ሱቁ ለ20አመታት ያህል ግለሰቦች በአነስተኛ ዋጋ የተለያዩ ለህብረተቡ የሚያገለግሉ ምርቶችን ሲያቀርቡ የነበሩ ምስኪኖችን አፈናቅሎ ለአንድ ፓስተር ባለቤት ለመስጠት ሁሉንም ውል ጨርሰዋል ብለዋል።
ቦታው ሊሰጣት ነው የተባለችው ግለሰብ ለቸርች ይገባኛል ብላ ጠይቃለች ስለዚህ በአስቸኳይ አስረክብ የተባለው የወረዳው ስራ አስፈጻሚ ደግሞ ማህበሩ የጀመረውን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሁሉ እንዲቋረጥ አድርጎ ቦታውን ሊሰጣት ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ግለሰቧ ይሄን ቦታ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በተጨማሪም ሁለትና ሶስት ቦታ የተሰጣት በእምነት ስም የምትነግድ ሴት ናት ሲሉ ገልጸዋል።
አቋርጦሞ የኅብረት ሱቁ በአካባቢ ሰዎች በኮሚቴ እየተሰራና ኅብረተ ሰቡን እያገለገለ የሚገኘውን ኮሚቴ ስራ አቁሙ ግንባታ ጠይቀው ፕላን አሰርተው ሊያስፋፉ ያሉትን ሁሉ በማገድ ከላይ ለጠቀስኩልሽ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከአንድ እስከ ሁለት ቦታ እየተሠጣት ላለች ነጋዴ ሊሰጣት ተዘጋጅቷል ሲሉ በመረጃቸው ላይ አስፍረዋል።