ኢትዮጵያን አስተዳድራለሁ ብሎ በሚያስበው የገዳዮቹ ስብስብ መካከል ከፍተኛ የሆነ ክፍፍል መፈጠሩን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አጋለጡ።
ከዚህ ክፍፍል ውስጥ ደግሞ አብይ አህመድ ስልጣኔን አለቅም ካለ በመፈንቅለ መንግስት መወገድ አለበት የሚል ቡድን መፈጠሩንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የአብይ አህመድ ቀኝ እጅ የሚባለውና በሰውዬው ዘንድ ትልቅ አመኔታ የሚጣልበት ሬድዋን ሁሴን ሳይቀር በሃሳብ መዋዠቅ መጀመሩን ይናገራሉ።
ላለፉት ሁለት ወራት ያህል ከነሬድዋን ጋር ሙሉ በሙሉ ግንኙነቱን ማቋረጡ ደግሞ በአመራሩ ዘንድ ከባድ የሆነ ጥርጣሬና ሌላ አማራጭን ወደ መፈለግ እንዲሄዱ እያደረጋቸው መሆኑንም ይናገራሉ።
ምናልባትም መፈንቅለ መንግስት እናድርግበት የሚለው ስብስብ እያየለ ከመጣ ምናልባትም ሁኔታዎችን ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊቀይረው ይችላል ሲሉም የውስጥ ምንጮቹ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
አሁን ላይ በፍርሃት እየራደ ያለው የገዳዩ ስርአት መሪ አሁን ላይ ቀጥታ ግንኙነቱ ከብርሃኑ ጁላና ከአበባው ታደሰ ጋር ብቻ ሆኗል ብለዋል።
አብዛኛውን ጊዜ ራሱን ለመደበቅና በራሱ ጭንቅላት ልክ ብቻ በማሰብ የጥፋት አጀንዳን የሚጠብቀው ግለሰብ ዛሬ ላይ ታማኞቼ ናቸው በሚላቸው አመራሮች ጭምር መፈንቅለ መንግስት እየታሰበበት ነው ሲሉ ሁኔታውን አስቀምጠዋል።
በተለይ በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀው የዘር ማጥፋት ጦርነት በሁሉም መስኩ አለመሳካቱ እንቅልፍ የነሳው ግለሰብ ራሱን መደበቅ ከጀመረም ሰንበት ብሏል ሲሉ ቤተመንግስቱ ውስጥ የተፈጠረውን ሽብር የውስጥ ምንጮቹ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
Comments