ደርባ የሚገኘው ከአዲስ አበባ በ45 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኘው ጫንጮ መሆኑን ይናገራሉ።
ፋብሪካው ስራውን ያቆመውም የኦነጉ ገዳይ ቡድን ከአንድ ወር በፊት እስከ ፋብሪካው ውስጥ ገብቶ አንድ ተርባይን በማቃጠሉ መሆኑን ያነሳሉ።
ተቃጠለ የተባለውም ተርባይን ከ5 ወር በኋላ ሊጠገን ይቻላል በሚል ፋብሪካው ስራውን እንዲያቆም መደረግንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ፋብሪካውን መዝጋት ብቻ ሳይሆን ከአንድ ወር በፊትም ሲሚንቶ ለመጫን ሲጠባበቁ የነበሩ ሹፌሮች ታግተው በብዙ ድርድር ያሉበትን ለማወቅና ለመደራደር ቢሞከርም እስካሁን ግን የመጣ አንዳችም ነገር የለም ብለዋል።
አሽከርካሪዎቹን ለማስፈታት በተደረገው ጥረትም ለእያንዳንዱ ሹፌር ማስፈቻም የተጠየቀው ገንዘብ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር መሆኑን ኢትዮ 360 በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ሸኖ ላይ በቅርቡም አንድ የህዝብ ማማላለሻ አውቶቡስ ሙሉ ተሳፋሪዎችን ያገተው ገዳይ ቡድን አፍኖ ከወሰደ በኋላ የት እንዳደረሳቸው አይታወቅም ይላሉ።
አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ይላሉ ምንጮቹ ባለሙያው ሆነ ሰላማዊ ዜጎች የመስራት አይደለም ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ ተፈጥሮአዊ መብቱንም ሙሉ በሙሉ ተገፏል ሲሉ ያለውን ስርአት አልበኝነት አመልክተዋል።
Comments