top of page

ነሐሴ 2/2015 በባህርዳር ከተማ ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን በጅምላ እየፈጀ ያለው የህወሃት ሃይል መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።



በባህርዳር ከተማ ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን በጅምላ እየፈጀ ያለው በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ አካባቢው እንዲገባ የተደረገው የህወሃት ሃይል መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።



ከዚህ ሃይል ጋር ደግሞ በሰው በላው ስርአት ታስረው የነበሩና በቅርቡ ከእስር የተለቀቁ የህወሃት ሃይል አባላት መካተታቸውንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።



ከምስራቅ እዝ መቀሌና ሽሬ ላይ ሃይል ሲያራግፍ የከረመው ሃይል የመቀሌውን ወደ ራያ የሽሬውን ደግሞ ወደ ደደቢት እንደሚልክ ኢትዮ 360 በመረጃው ይፋ ማድረጉን ያስታውሳሉ።



በመቀሌ እንዲራገፍ ከተደረገው ሃይል አብዛኛው ደግሞ በእስር ቤት የከረመውና ሁለቱ ገዳይ ቡድኖች እርቅ አውርደናል ማለታቸውን ተከትሎ ከእስር የተለቀቀ ነው ሲሉም ያነሳሉ።



ትላንት ምሽት ላይ ከጋሸና ወደ ወልድያ አለፍ ብሎ ሻለቃ ፈንታው ሙሀባው ጋር የገጠመው የገዳዩ ቡድን ወደ ኋላ መሸሹን ይናገራሉ።



ነገር ግን ወደ ኋላ የሸሸበት ዋና ምክንያት አግዝሃለሁ ብሎ ወደ እሱ እየመጣ የነበረ የገዳዩ ስርአት ሃይል በህዝባዊ ሃይሉ ሃይል አይቀጡ ቅጣት በመቀጣቱ ነው ይላሉ።



ሽንፈቱን ከተከናነበው ቡድንም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች መማረካቸውንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።


የአማራ መገናኛ ብዙሃን ስርጭት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መቋረጡንም ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።



በዚህ ሰአት ወደ ስርጭት አለመመለሱን ምንጮቹ እየተናገሩ ባሉበት ሰአት የአሚኮ ቴሌቪዥን በመጠነኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የስርጭት የጥራት መጓደል ገጥሞት ባለሙያዎቻችን እንዲስተካከል ተደርጓል የሚል አስቂኝ ማስታወቂያ ማውጣቱን ይናገራሉ።



በውስን የራዲዮ ማሰራጫዎች(ትራንስሚተር)ላይ በኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት ስርጭታቸው መቆራረጥ አጋጥሟል በአጭር ጊዜ ውስጥም የተሟላ ስርጭት እንዲኖር አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ ነው የሚል ነገርም ታክሎበታል።



ኢትዮ 360 በትላንት ዛሬ ምናለ የቀጥታ ስርጭቱ በመገናኛ ብዙሃኑ ውስጥ ሁለት ቴክኒሻን ብቻ አስቀርተውና የተመስገን ጥሩነህ ቀኝ እጅ በሆኑት የዜና ክፍል ሃላፊውና ምክትሉ ብቻ እየተሰራ መሆኑን ማጋለጡ ይታወሳል።



ይመለስ አይመለስ የታወቀ ነገር የለም ሲሉም ምንጮቹ አመልክተዋል።



የአማራ ራዲዬ ስርጭት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል በአሁኑ ሰአት ወደ ስርጭት ይመልስ አይመለስ የታወቀ ነገር የለም።



በየቦታው ሽንፈት ቁርሱ የሆነው የሰው በላው ስርአት ሃይል በወሎ በኩል ከደሴ ወደ ምዕራብና ሰሜን ወሎ ብዛት ያለው ተጨማሪ ሃይል እያጋዘ መሆኑም ምንጮቹ አመልክተዋል።



አቀስታ፣ ገነቴ፣ መካነ ሰላም፣ ወገልጤና ፣ ወረኢሉና አካባቢው ያለው ማህበረሰብ ይሄንን ገዳይ ቡድን ባለበት እንዲያቆመውም ጥሪ ቀርቦለታል።



በሰሜን ሸዋም ተከታታይ ውርደት የተከናነበው ገዳይ ቡድን ወደ ደብረብርሃን ከተማ ከ60 አውቶቡሶች በላይ ወታደሮችን፣ታንኮችንና ከባድ መሳሪያዎችን ማስገባቱንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።



በተመሳሳይም ሰሞኑን በህዝባዊ ሃይሉ ነጻ የወጣችውን የሸዋ ሮቢት ከተማን ዳግም ለመቆጣጠር ይሄው ቡድን ጦርነት መክፈቱንም ተናግረዋል።



ወደ ከተማውም በተለይ ደግሞ ንጹሃን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ እያስወነጨፈ መሆኑንም ነው የኢትዮ 360 ምንጮች ያመለከቱት።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page