ነሐሴ 2/2015 በአርባምንጭና በሌሎች አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃሞው እንዲቀጥል ማደጉን የአርባምንጭ ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
- Ethio 360 Media 2
- Aug 8, 2023
- 1 min read
የደቡብ ክልል አዲሱ የክላስተር አደረጃጀት ዛሬም በአርባምንጭና በሌሎች አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃሞው እንዲቀጥል ማደጉን የአርባምንጭ ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
የአርባምንጭ ነዋሪ አደባባይ በመውጣት ጭምር ክህደት ተፈጽሞብናል በሚል ድምጹን ማሰማት ቀጥሏል ብለዋል ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ።
የህዝቡ ጥያቄ ክላስተር ሳይሆን የራሱን ክልል መመስረት አልያም አርባምንጭን ማዕከል ባደረገ መልኩ ከጋሞ ህዝብ ጋር በስነልቦና ተመሳሳይ ከሆኑ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩ አደረጃጀቶች ግጭት ካልተፈጠሩ ህዝቦች ጋር ክልል መመስረት ነው ሲሉም አስቀምጠዋል።
ይሄ ሆኖ ሳለ ታሪክንም ሳይንስንም በዘነጋ ሁኔታ እንደከዚ ቀደሞቹ አደረጃጀቶች ህዝቦችን ወደ ግጭትና እልቂት የሚያስገባ አደረጃጀት ይፋ ተደርጓል ሲሉም አስምረውበታል።
ነገር ግን ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ እያሰማ ባለበት በዚህ ሰአት በከተማው የሚገኙ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ከእሁድ ምሽት ጀምሮ እስከ ትላንት ሰኞ ድረስ ወጣቶችን ቤት ለቤት በመሄድ በመያዝና በማሰር ብሎም በመደብደብ ላይ ይገኛሉ ሲሉም በመረጃቸው ላይ አስፍረዋል።
ነገር ግን እስርና ድብደባ ያላስፈራው ህዝብ ዛሬም በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄውን በማቅረብ ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ዛሬ አደባባይ የወጣው ህዝብ ቁጣ ያስፈራው ስብስም አፍኖ የወሰዳቸውን ወጣቶች መልቀቁንም ተናግረዋል።
ነገር ግን ተቃውሞ ይነሳል ሰልፍ ይደረጋል በማለት የሰጋው ገዢ ስርዓት ከተማዋን በፌደራልና በመከላከያ ሰራዊቶች እንድትወረር አድርጓታል ሲሉ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ አስፍረዋል።
በጋሞ ዞን ከምባ ወረዳ የታሰሩ ወጣቶች ግን እስካሁን ከታሰሩበት አለመለቀቃቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።