top of page

ነሐሴ 2/2015 በደብረዘይትና አካባቢው ወጣት አዋቂን ያለየ ከባድ አፈና በጅምላ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


በደብረዘይትና አካባቢው ወጣት አዋቂን ያለየ ከባድ አፈና ከትላንት ጀምሮ በጅምላ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።



በሰላሙ ጊዜ ወደ አካባቢው የገባው የአማራ ተወላጅ አሁን በየቤቱ እየታደነና እየታፈነ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።



የሚታፈነው ሰው ከመብዛቱ የተነሳ ማሰሪያ ቦታ አልበቃ ብሎ በየቦታውም ነዋሪው እየታጎረ መሆኑን ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።



የነዋሪውም ሆነ የመጓጓዣ አገልግሎት የተቆጠበ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ከሰአቱ በላይ ደግሞ ፍተሻው በጣም የከፋ ነው ይላሉ።



ለሊት ላይ መቶ ከቤት አፍኖ የሚወስደው አካል ነዋሪውን ወዴት እንደሚወስደው እንኳን አይታወቅም ሲሉ ይገልጻሉ።



አሁን ላይ ህብረተሰቡ እየደረሰበት ካለው ግፍ አኳያ የአማራ ህዝባዊ ሃይልን መቀበል ብቻ ሳይሆን መሳሪያ ከማንሳት ራሱ ወደ ኋላ የለም ሲሉ የህዝቡን ምሬት ይናገራሉ።



ስብስባ የጠራቸው አካል ለምን እንደጠራቸው እንኳም ማወቅ እንዳልቻሉ ይናገራሉ።



አካባቢያችሁን ጠብቁ በሚል አጀንዳ ይዞ የሚመጣው አካል በረሃብ፣በስራ እጦትና በተለያዩ ችግሮች እየተሰቃየ ያለውን ማህበረሰብ ሊረዳው አልቻለም ብለዋል።


አሁን ላይ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች እጅግ የሚጸየፉት አካል ቢኖር ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ የሚለውን ገዳይ ቡድን ነው ይላሉ።



ምናልባትም ከፍተኛ ሃይል አለኝ ብሎ የሚያስበው አካል እየሄደበት ያለው አካል በፓትሮል በመዞር ጭምር ነዋሪውን እያሸበረው ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።



በቅርቡ ከኦነግ ጋር እስር በርሱ ሲዋጋ የከረመው የሰው በላው ስርአት ስብስብ ህብረተሰቡን በዚህ መልኩ ሲያሰቃየው ነበር ይላሉ።



በአካባቢው ያሉ ወረዳዎችን ይሄው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ እንዲመራ ያደረገው አካል የአካባቢውን ወረዳዎች እንዲያስተዳድር ተደርጓል ይላሉ።


ሌላው ይላሉ እርስ በርሱ መስማማት የማይችልና አላማ የሌለው አካል ነው ሃገርና ህዝብን እያመሰ ያለው ሲሉም እውነተኛ ገጽታቸውን ያጋልጣሉ።



እርስ በርሳቸው ከመከፋፈላቸውም በላይ ሌብነታቸው ደግሞ አይን ያወጣ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page