በናዝሬት አዳማ አባ ገዳ አዳራሽ አዳነች አበቤ በጠራችው ስብሰባ ላይ የተገኙ የብአዴን አመራሮች እየተለቀሙ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
በዚህ ስብሰባ ላይ ከ2ሺ በላይ አመራሮ እንዲገኙ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ እስካሁን ከ58 በላይ የብአዴን አመራሮችሰባ ከዛው ስብስባ ላይ ታፍነው በፓትሮል ተጭነው መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
ከታፈኑት ውጪ ያሉትና በስብሰባው ላይ የሚሳተፉት የብአዴን አመራሮች ደግሞ ቤታቸው እየተፈተሸ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ አይን ያወጣ የዘር ተኮር ጥቃት እየተፈጸመ ነው የሚሉት ምንጮቹ በተለይ የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረው የዘር ተኮል ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን ለእስርና ለድብደባ ዳርጓቸዋል ይላሉ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ከመማሪያነት ወተው ለንጹሃን ዜጎቹ ማጎሪያ ሆነዋል ሲሉም ምንጮቹ አስምረውበታል።
አዳነች አበቤን ተከትሎ ስብስባ በሚል ናዝሬት የከተመ ብአዴን ሁሉ ቀጣይ እጣ ፋንታው መታፈንና መገደል ነው ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።