በሰራዊቱ ውስጥ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ አፈና ለማካሄድ እቅድ መያዙን የኢትዮ 360 ምንጮች አጋለጡ።
በተለይ ደግሞ በአማራ ህዝብ ላይ ባወጀው ጦርነት ሽንፈት እየተከናነበ ያለው አካል የሚያደርገው ጠፍቶት ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል ብለዋል።
ድንጋጤውን ያባሰበት ደግሞ የአማራ ህዝባዊ ሃይል እስከ መሃል ሃገር ገፍቶ ከመጣ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው የአማራ ተወላጅ ቀድሞ እርምጃ ይወስድብኛል በሚል መሆኑንም አስምረውበታል።
ስለዚህም ይሄ ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ በሰራዊቱ ውስጥ ያሉ የአማራ ተወላጆችን ማፈን የሚለው ዋና አጀንዳ ሆኖ ተቀምጧል ይላሉ።
ይሄንን ለማሳካት ደግሞ በእያንዳንዱ የሰራዊቱ አባል በሆነ የአማራ ተወላጅ ላይ እንቅስቃሴውን ሁሉ የሚከታተል ሰላይ ተመድቦለታል ብለዋል።
ይሄውንን ጥናት ከጨረሱ በኋላም በቀጥታ በያሉበት ማፈን የሚለውን በቅርቡ ተግባራዊ ለማደግ ተስማምተዋል ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ ተናግረዋል።
ምናልባትም በዚህ መሃል ደግሞ የደቡብና የአዲስ አበባ ልጆችም መስዋኦት ሊደረጉ ይችላሉ ሲሉም የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
Comments