top of page

ነሐሴ 2/2015 የጎንደር ከተማን በከባድ መሳሪያ እያወደሙዋት ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።ከወልቃይት የተነሳውና በሌላኛው ባንዳ ጄኔራል ዋኘው አለሜ የሚመራው ኮር የጎንደር ከተማን በከባድ መሳሪያ እያወደማት ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።የዋኘው አለሜ ጦር ከወልቃይት ተነስቶ ጎንደር ከተማ እንዲመጣ የተደረገው በባንዳው ብርጋዴር ማርየ በየነ የሚመራው 105ኛ ኮር በህዝባዊ ሐይሉ በማደከሙ ነው ሲሉም ምንጮቹ ተናግረዋል።የተወሰኑ ብረት ለበስ እና አንድ ታንክ አስተዳደርና ፓሊስ ጣቢያ ገብተው እየተኮሱ ባለበት ሰኣአት ህዝባዊ ሃይሉ 1 ብረት ለበስ ከነተኳሾቹ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጨምረው ገልጸዋል።


ዛሬም የህዝባዊ ሃይሉን መቋቋም ያልቻለው ገዳይ ቡድን በውትድርና ሳይንስ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሞርተር ከተማውንና ንፁሐኑን ህዝብ እየፈጀ ነው ሲሉም አስቀምጠዋል።በብልኮኮ፣ ፒያሳ፣ ቀበሌ 18 ፣ዩንቨርሰቲ፣ ቀሐ ወንዝና አንገረብ አካባቢ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን መጨፍጨፉንም ይናገራሉ።


ይሄንን ጨፍጫፊ ቡድን ለማገዝ ከአብደራፊ ሲመጣ የነበረ ተጨማሪ የጠላት ሐይል በሙሴ ባንብና ማርዘነብ ታች አርማጭሆ በህዝባዊ ሃይሉ ተቆርጦ ቅጣቱን እየተቀበለ ነው ሲሉም ህዝባዊ ሃይሉ እየሰራ ያለውን ጀግንነት ይመሰክራሉ።


በዚህ ሁሉ ውጊያና የአማራ ህዝብ በዚህ ደረጃ እየተወረረና እየተገደለ ባለበት ሰአት ደግሞ አሁንም ያላረፉና የገዛ ወገናቸውን ለማስበላት የሚሰሩ የብአዴን ርዝራዥ ሆድ አደር ስብስቦች መኖራቸውን የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ይናገራሉ።


ህዝባዊ ሃይሉ ግን እያደረገ ያለው ተጋድሎ መጨረሻው ድል ነው ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


ይሄው የሆድ አደሩ ቡድን ያልመረጠውን ህዝብ ወክሎ ድርድር በሚል እንደሚቀመጥም ሳይናገሩ አላለፉም።


ይሄው የሆድ አደሩ ስብስብ ገዳዩን ቡድን ልብሱን አስቀይሮ እስከማስገባት የደረሰ አሳፋሪ ተግባር እየፈጸመ መሆኑንም ገልጸዋል።


ለህዝባዊ ሃይሉ አቅም የሚሆንና በማክሰኝትና በሌሎች አካባቢዎች የሚንቀሳቀስና አጼ ሰርጸ ድንግል የሚባል አዲስ የፋኖ ግንባር መመስረቱንም የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ይናገራሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎንደር ከተማ ወጣት በባዶ እጁ አድማ በታኝና ሚሊሻ የሚኖሩበት አካባቢ ማጽዳቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ገነት ተራራ ጉሃ ሆቴል፣ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ደብረብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን ጀርባ መሽጎ የተቀመጠዉ ወታደር ዛሬ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ከአቡነ አረጋዊና ደብረብርሃን ስላሴ አካባቢ የነበረዉን ወታደር ተበትኖ እንዲፈረጥጥ መደረጉንም ገልጸዋል።ሆኖም በተለያዩ የጎንደር ከተማ የተለያዩ አካባቢውች ባታዎች ለመግባት ጥረት ያደረገው ገዳይ ቡድንም በህዝባዊ ሃይሉ ከጥቅም ውጪ ሆኗል ብለዋል ምንጮቹ።ነገር ግን የከተማዉ አመራሮች መሽገዉ የተቀመጡበት ፖሊስ መምሪያና ገነት ተራራ የመሸጉ ወታደሮችን ማጥቃት የህዝባዊ ሃይሉ ስራ ሆኗል ብለውል።እንዲሁም ጎንደር ዮኒቨርስቲ ቴድሮስ ካምባስ ተደብቆ የነበሩ ወታደሮች ቀራኔዮ መዳኒዓለም ተራራ ላይ መሽገው እንደሚገኙም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።የጎንደር ከተማን ሆን ተብሎ መብራት ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Commentaires


bottom of page