(ኢትዮ 360 - ሐምሌ 13/2015) ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ከሃገሩ ተሰደደ።
- Ethio 360 Media 2
- Jul 20, 2023
- 1 min read
በተደጋጋሚ በገዳዩ ስርአት ማፈኛ ቤቶች እንዲማቅቅ የተደረገው ጋዜጠኛ ቴድሮስ አስፋው አሁን ባለው ሁኔታ በሃገር ውስጥ የሚያንቀሳቅስ ነገር ባለመኖሩ የሚወዳት ኢትዮጵያንና የሚወደውን ሙያውን ትቶ ለመሰደድ መገደዱን ለኢትዮ 360 ገልጿል።
በተደጋጋሚ በሚያሳቸው ሃሳቦችና የገዳዩ ስርአትን በአደባባይ በማጋለጥ የሚታወቀው ጋዜጠኛው በተደጋጋሚ በታፈነበት ወቅት ያደርሱበት የነበረው የሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ የመብት ጥሰትና እውነትን ለማፈን የደረግ የነበረው ርብርብ እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ እንዳደረገውም ተናግሯል።
ጋዜጠኛ ቴድሮስ አስፋው ከሐገር መውጣቱ ጋር ተያይዞ ለኢትዮ 360 በሰጠው መረጃ እንደ ሃገር ያለው ሁኔታ የማያሰራ ብቻ ሳይሆን ለህይወት አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ በመድረሱ ከሃርገ ለመኮብለል መገደዱን ነው የተናገረው።