top of page

(ኢትዮ 360 - ሐምሌ 19/2015)በምዕራብ ደንብያ የሰው በላው ስርአት ሃይል በንጹሃን ላይ ጦርነት ከፈተ።


በጎንደር ምዕራብ ደንብያ ጯሂት ከተማ የሰው በላው ሰራዊት በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ጦርነት መክፈቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


የኦዴዱ ሃይል ጠዋት ላይ በጎርጎራ በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሃይል ሲያግዝ መቆየቱን ይናገራሉ።

የሃይሉን ብዛት ያየው ነዋሪም አታልፉም በሚል መንገድ መዝጋቱንና ከዚሁ ሃይል ጋር ፊት ለፊት ተፋጦ ማርፈዱን አመልክተዋል።


ነገር ግን ከባድ መሳሪያ ጭምር የያዘው የሄው የገዳዮቹ ስብስብ ንጹሃንን በመጨፍጨፍና ሰላማዊ ሰዎችን እየጨፈለቀ ወደ አካባቢው መግባቱን ይናገራሉ።


አሁንም ይሄንን ገዳይ ቡድን ፊት ለፊት እየተጋፈጠው ያለው የአካባቢው ማህበረሰብ ከተለያዩ አቅጣጫ ያሉ መንገዶችን በመዝጋት እዳያልፍ እያደረገው መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


የአማራ ፋኖ በጎንደር የምኒልክ ብርጌድም የሄው የገዳዩ ስርአት ሃይል በቆላድባ ደረስጌ ማርያም አካባቢ ተኩስ እንደከፈተበትም በይፋ ተናግሯል።


ብርጌዱ ከጎንደር በኩል አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግለትም ጥሪውን ማቅረቡንም ገልጸዋል።


በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ከጯሂት በቅርብ ርቀት በህማህበረሰቡ እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ላይ በዲሽቃ የታገዘ ተኩስ መከፈቱንም አንስቷል።


ይሄን ተከትሎም ለድጋፍ በእንቅቃሴ ላይ የሚገኘው የአማራ ፋኖ በጎንደር የምኒልክ ብርጌድ ደረስጌ ማርያም ላይ ከባድ ተኩስ እንደተከፈተበት መግለጹንም አመልክተዋል።


ድጋፍ እንዲደረግለትም ጠይቋል ሲል አማራ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

በሌላ በኩልም የኦህዴዱ ገዳይ ቡድን ከሰሜን ወሎ መርሳ ከተማ ተነስቶ አምባሰል አካባቢ ያለውን ፋኖ ለማፈን ወደ አካባቢው እያመራ መሆኑንም ጠቁመዋል።


የአካባቢው ወጣትና የመርሳ ከተማ ማህበረሰብ ከፋኖዎች ጎን እንዲቆሙ ጥሪ መተላለፉንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


ይሄው ገዳይ ስርአት ወደ አማራ ሳይንት እገባለሁ ካለ ደግሞ ጦርነቱ በለጩማ ላይ ያልቃል ሲል የወረዳው አስተዳዳሪ በግልጽ መናገሩንም አመልክተዋል።


ከየአካባቢው አሁን ላይ ይሄንን ገዳይ ቡድን ፊት ለፊት የሚጋፈጡ የብአዴን አመራሮች መኖራቸውን የሚናገሩት ምንጮቹ የዛንው ያህል ደግሞ ወገናቸውን ለመጨረስ እየታገሉ ያሉ እንደነጄኔራል አበባው ታደሰ አይነቶቹ ሆድ አደሮች ደግሞ ጦር ማጋዛቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።


በአካባቢው ይሄ ገዳይ ቡን መግባቱን ተከትሎ ደግሞ የኢትዮ ቲሌኮሟ ፍሬህይወት በአካባቢው ኢንተኔት በማቋረጥ ለገዳዩ ሰአት የተለመደ ድጋፏን እየሰጠች ነው ሲሉም ምንጮቹ ተናግረዋል።


በአይን ጥቅሻ የሚግባባው የፋኖ ህዝባዊ ሃይልና ማህበረሰቡ ግን ኢንተርኔት ሳያስፈልገው በጋራ ሆኖ ይሄንን ገዳይ ስርአት ለመከላከል የሞት የሽረት ትግሉን እያደረገ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Email: ethio360dgre@gmail.com

Phone: 540-277-3242

Donate with PayPal

© 2023 by Ethio360 Media

Connect with Us

  • rumble
  • Telegram
  • TikTok

Support Us

Advertise With Us

bottom of page