በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርት የሚያድስላቸው አካል በማጣታቸው ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ፓስፖርት ለማሳደስ ኤምባሲውን ሲለምኑ ወደ ሰባት ወራትን ማስቆጠሩን ይናገራሉ።
ከኤምባሲው ጠብቁ የሚሉ ተደጋጋሚ ምላሾች ቢሰጡም እስካሁን ግን በመጠበቅ የተገኘ ነገር የለም ብለዋል።
እስከ ሰኔ 30 ፓስፖርታችሁ ታድሶ ይመጣሉ የሚል ቃል ተገብቶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ግን ምንም ሊያደርጉ አልቻሉም ብለዋል።
ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ለኤምባሲው በሰጡበት እዛው የመገልገያ ጊዜውን እንደተቃጠለም ሳይገልጹ አላለፉም።
ነጭ ወረቀት ሰቶ በእሱ ተጠቀሙ የሚለው ኤምባሲ በራሱ መፍትሄ ለማምጣት አልቻለም ብለዋል።
አምባሳደሩን ጭምር አናግረናል የሚሉት ኢትዮጵያውያኑ ነገር ግን ማንም የመፍትሄው አካል ሊሆን ባለመቻሉ ኢትዮጵያውያኑ በአሰሪዎቻቸው ያለምንም ማስረጃ እየተጫኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
በሰው ሃገር ያለፓስፖርት መንቀሳቀስም ሆነ የቤት ኪራይ መክፈልም ሆነ የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደማይቻል እየታወቀ ማንም ግን ሊያግዛቸው እንዳልቻለ ነው ለኢትዮ 360 የገለጹት።