የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ በወንጀል የሚፈለጉትን ጨምሮ ሁሉም የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላት ደብረብርሃን ላይ ለውይይት እንዲከቱ በሚል ለካቢኔው አባላት አስቸኳይ ትእዛዝ መስጠቱን የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ሰሞኑን ቤቱ በቦንብ የተደበደበበት የዞኑ አስተዳዳሪ ፋኖን ሰብስቦ ማነጋገር በክልል ደረጃ የተቀመጠ ነው በሚል መመሪያውን ማውረዱን ይናገራሉ።
የካቢኔው አባላት ደግሞ ላሉት ወረዳዎች ሁሉ መመሪያውን እንዲያስተላልፉ ነው ትእዛዝ የተሰጣቸው ብለዋል።
ጨዋታቸው አይጠገብም በሚል የተሳለቁባቸውን የፋኖ ህዝባዊ ሃይሉ አባላት ከሁሉም የሚያስቀው ደግሞ ትእዛዝ የተሰጠው ካቢኔ ፈንጠዝያ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገለጸዋል።
በህዝብም በፋኖ ህዝባዊ ሃይል ላይ ክህደት የፈጸመው የደብረብርሃን ከንቲባም ወደ ክልል ለመግባት ከሚያደርገው ጥረት ባለፈ ሃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው በለቀቁ አመራሮች ቦታ ሌላ ለመተካት እየሰራ ነው ብለዋል።
እነሱም እንደሸዋ ህዝባዊ ፋኖ የወሰዱትና ያስቀመጡት አቅጣጫ መኖሩንም ጠቆም ሳያደርጉ አላለፉም።
Comments