በአዲስ አበባ ከተማ የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ያለ እሽግ ቆሎ በስተቀር ሌላ ምንም አይነት ምግብ ይዘው እንዳይገቡ መከልከሉን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ከዛም አልፎ አሁን ሃገሪቱ ያለችበት ሁኔታ እየታወቀ አንድም የእጅ ስልክ ይዘው እንዳይገቡና ከቤተሰቦቻቸውም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው ተደርገዋል ሲሉ ምንጮቹ ተናገረዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎቹ ከእሽግ ቆሎ በስተቀር ምንም ይዘው እንዳይገቡ የተደረገበት ምክንያት ደግሞ በየመፈተኛ ጣቢያው ባለጊዜዎች የምግብ ቤቶችንንና የሻይ ቤቶችን ንግድ ጠቅልለው እንዲይዙ በመደረጋቸው መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህም በላይ የሚያስገርመው ነገር ይላሉ ምንጮቹ ተማሪው ገዝቶ እንኳን እንዳይበላ አንድ ተራ በርገር ከ500እስከ 1000 ብር በመሸጥ ላይ ሲሉ እየተሰራ ያለውን ግፍ ይናገራሉ።
አሁን ባለው ሁኔታ ምናልባትም የባለጊዜዎቹ ልጆች ይሄንን በርገር ሊበሉ ይችሉ ይሆናል እንጂ ድሃው ተማሪ ግን እንኳን በርገር ገዝቶ ሊበላ ቀርቶ የተሻለ ሽሮ እንኳን ማግኘት ብርቅ ሆኖበታል ሲሉ ያለውን እውነታ አስቀምጠዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎቹ ወደ መፈተኛ ጣቢያው ከገቡ በኋላ ወዴትም መውጣት እንዳይችሉ ያደረገው የፕሮፌሰር ብርሃኑ አስተዳደር ገና ወደ ግቢው ሲገቡ በኦህዴዱ ሃይል ታጅበው እንዲገቡ እስከማድረግ ደርሷል ይላሉ።
ተማሪዎቹ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት ለተመለከተው የተፈታኞቹ አያያዝን ላየው በየአካባቢው በግፍ ታፍነው የተወሰዱ የህሊና እስረኞችን እንጂ ለፈታና የሚሄዱ ተማሪዎችን አይመስሉም ሲሉም እውነታውን ገልጸውታል።
ተማሪዎቹ ዙሪያውን ታጅበው ሲሄዱ ወላጆቻቸው ደግሞ በቅርብ ርቀት ቁመው ልጆቻቸውን በእጅ ሰላምታ ብቻ ሲሰጣጡና ወለጆች አይናቸው በእንባ ተሞልቶ ስታይ ልጆቻቸውን ወደፈተና ሳይሆን ወደጦር ግንባር አልያም ወደ ብሔራዊ ውትድርና የሚሸኙ ቤተሰቦች ናቸው የሚመስሉት ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች አሳዛኙን ሁኔታ ገልጸውታል።
አሁን ትምህርት ሚኒስቴርን እመራለሁ የሚለው ፕሮፌሰር ብርሃኑ የኢትዮጵን ሥርዓተ ትምህርት ከድጡ ወደማጡ ወስዶ በአፍ ጢሙ እየተከለው ነው ብለዋል።
ፕሮፌሰሩ በተማሪዎችና በስርአተ ትምህርቱ ላይ እየሰራ ላለው ወንጀል ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በአራት ኪሎ ዩኒቨስቲ ትልቁን ውርደት ተከናንቦ ተመልሷል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ባለፈው ሰኞ ተማሪዎችን እንኳን ገባችሁ ለማለት 6 ኪሎ አካባቢ ወደ ሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲ ያቀናው ብርሃኑ ተማሪዉ በስድብና በጩህት ሲያባርረው ወደ 4 ኪሎ ዩኒቨርስቲም ሲያቀና የጠበቀው ተመሳሳይ ነገር ነው ብለዋል።
የተማሪው ጩህት ያስደነገጠው ፕሮፌሰሩ ጆሮውን ይዞ ከመውጣት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻለም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።