ራያና ጠለምትን በሰው በላው ስርአት ሃይል ስር ለማድረግ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አመለከቱ።
የክልሉ ካቢኔ አሳልፌያለሁ የሚለውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በየዞኑ አመራሩ በየደረጃው ስብሰባ ተጠርቶ እንደነበር ይናገራሉ።
ነገር ግን የብአዴኑ ሆድ አደር ቡድን ባሰበው ደረጃ እቅዱን ማሳካት እንዳልቻለም አመልክተዋል።
ምክንያቱ ደግሞ ሁሉም አመራር በሚባል ደረጃ በካቢኔ ተወሰነ የተባለውንና ራያና ጠለምትን በሰው በላው ሃይል ስር እናደርጋለን የሚለውን ውሳኔ በመቃወማቸው መሆኑን አንስተዋል።
በተለይ በዋናነት የዞን አመራሮች፣ ከንቲባና ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሃላፊወች በተገኙበት ስብስባ ላይ ተሰብሳቢው በግልጽ አቋሙን በማሳወቅ ሃሳቡን ውድቅ አድርጎታል ብለዋል።