በፍቼ ሰላሌ በሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ በሲሚንቶ ጥበቃ ላይ የነበሩ ከ20 በላይ የትላልቅ ተሽከርካሪ ሹፌሮች በኦነግ ገዳይ ቡድን መታገታቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ይሄው ገዳይ ቡድን በእያንዳንዱ ሰው እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
እነዚህ የትላልቅ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮች ማንነታቸው ስለሚታወቅ ብቻ ጉዳዩ ይፋ ሆነ እንጂ በየቀኑ በዚሁ ቡድን የሚታገቱ ንጹሃን ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በተመሳሳይ ይላሉ ምንጮቹ በአዋሽ ወለንጪቴ መስመር ላይም ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል ብለዋል።
ከሁለት ቀን በፊትም ሙሉ ሙሉ ታታ አውቶቡስ ተሳፋሪ በዚሁ ገዳይ ቡድን መታገቱን ይናገራሉ።
በአውቶቡስ ውስጥ የነበሩትና በዚሁ ገዳይ ቡድን የታገቱ ሰዎች ቁጥርም ከ45 እስከ 60 ይደርሳል ሲሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
በሁሉም አቅጣጫ ገዳይ ቡድኑን እያሰማራ ያለውና ቤተመንግስቱን የተቆጣጠረው ስብስብ አሁንም በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰው አፈና፣ግድያና ማሳደድ ቀጥሏል ሲሉም ምንጮቹ ገልጸዋል።
Comments