የደቡብ ክልልን የመጨረሻ እጣ ፋንታ የሚወስነው የምክር ቤቱ ስብሰባ ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በክልሉ ባሉ ሆድአደር አመራሮች ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የቀድሞ ደቡብ ክልል የመጨረሻ ስብሰባ ከመጪው ዓርብ ጀምሮ ይካሄዳል እንደሚካሄድም ምንጮቹ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ አስቀድሞ ስብሰባውን ሊያደርግ የነበረው ከሐምሌ 9 እስከ 10/2015 እንደነበርና ላልተወሰ ጊዜ በሚል ማራዘሙን አስቀምጠዋል።
ነገር ግን የመጨረሻው ስብሰባ እንዲዘገይ የተደረገበት ዋናው ምክንያት ግን የአዲሱ ክልል መቀመጫ የት ይሁን በሚለው ጉዳይ ባለምስማማታቸው፣ በስልጣን ክፍፍል እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ሊግባቡ ባለመችላቸውን ነው ሲሉ ያስቀምጣሉ።
በተለይም ደግሞ በክልሉ ብልፅግናው ፅ/ቤት ኃላፊ የአቶ ጥላሁን ከበደ ቡድን የኦህዴዱን ቡድን አቅጣጫ አልቀበልም በሚል በማፈንገጡ ነው ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።
ከዚህ ሁሉ ውዝግብ በኋላም የክልሉን የመጨረሻ ስብሰባ ከሐምሌ 28-30/2015 ዓ.ም ለምካሄድ ከስምምነት መደረሱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በዚህ የመጨረሻ ስብሰባም የአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጉዳይ የመጨረሻ እልባት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።
ቀሪው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም የራሱን ክልላዊ መዋቅር መልሶ ለማደራጀት የመጨረሻውን መለያየት የሚያደርጉበት ጉባኤ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
Comments