የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ በየቦታው የተመደቡ ተማሪዎች በረሃብና በእንቅልፍ እጦት እየታመሙ መሆኑን ወላጆቻቸው ለኢትዮ 360 አስታወቁ።
ለተማሪዎቹ ፕሮሰር ብርሃኑ ነጋ ያወጣው መመሪያ ተማሪዎቹን ለከፋ ጉዳት እየዳረገ ነው ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።
በዚህ ሁሉ ድብደባና ስቃይ ውስጥ ደግሞ ተማሪዎቹ የሚያርፉበት ቦታም የለም ሲሉም ይናገራሉ።
ፈተና በሚባል ሰበብ በአንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ከ15ሺ በላይ ተማሪዎችን በማሸግ በህይወታቸው እየቀለደ ነው ሲሉም ይከሳሉ።
ብርሃኑ ነጋ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መጠየቅ አለበት የሚሉት ወላጆች ልጆቻቸው ላይ ከሚደርሰው የከፋ ችግር ጋር ተያይዞም ልጆቻቸውን ወደ ሆስፒታል ሲያግዙ እንደሚያደሩም ይገልጻሉ።
እንቅልፍና የምግብ እጦት እየተሰቃዩ ስላሉት ልጆቻቸውም ሁሉም ወላጆች ሊጠይቁ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።