በሰሜን ሸዋ ቡልጋና አካባቢው የአማራውን ትግል እየጎተቱና እያስበሉት ያሉት የብልጽግና ካድሬዎች መሆናቸውን የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በተለይ ሰሞኑን ስማቸው በግልጽ ከተነገረው ውጪ ዋናውና በጀት በመመደብ ጭምር የራሱን ወገን ለማስጨረስ የሚንቀሳቀሰው የቡልጋ ከተማ ከንቲባ ብርሃኑ መኮንን መሆኑን ያጋልጣሉ።
የሆድ አደሮቹ ስብስብ በዝርዝር ስማቸው ሲወጣ የዚህ አደገኛ ሰው ስም ግን ተዘሏል ብለዋል።
ይሄንን ወንጀል ሲፈጽም ደግሞ ከመንግስት ካዝና የሚወጣ የህዝብ ገንዘብን በመዝረፍ ጭምር ነው ይላሉ።
በአማራው ትግል ውስጥ ትልቅ ችግር ከሚፈጥሩና እንቅፋት ከሚሆኑት መካከል ይሄ ግለሰብ አንዱ መሆኑን ሁሉም ሊያውቀው ይገባል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።