top of page

(ኢትዮ 360-ሐምሌ 4/2015) በአዲስ አበባ በኮዬ ፈጬ አካባቢ ያሉ የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከባለንብረቶቹ ሊነጠቁ ነው።


በአዲስ አበባ በኮዬ ፈጬ አካባቢ ያሉ የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለሪል እስቴት ይፈለጋሉ በሚል ነዋሪዎቹን ቤታቸውን ሊነጥቋቸው መዘጋጀታቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


የ10/90 ባለእድሎች 10 በመቶውን ቅድሜያ ከፍለው የቀረውን ደግሞ በየጊዜው ለባንክ እየከፈሉ እንዲኖሩ ለማድረግ የተሰሩ መሆናቸውን ያነሳሉ።


ነዋሪውም የሚጠበቅባቸውን ከከፈለሉ በኋላ ከባንክ የተበደሩትን እዳ በየጊዜው እየከፈሉ በጋራ መኖሪያ ቤቱ መኖር ከጀመሩ ወደ አምስት አመት እንደሆናቸውም ይናገራሉ።


አሁን ግን ሰው በላው ስርአት አምስት አመት ሙሉ ገንዘባቸውን ሲከፍሉ የኖሩበትን ቤታቸውን ሊነጥቃቸው ከዳር ደርሷል ብለዋል።


ነዋሪውን ከገዛ ቤቱ አስወጥቶ በረንዳ ላይ ለመጣል የተዘጋጀው ለሌላ አላማ ሳይሆን ለባለጊዜዎች ሪል እስቴት መገንቢያ በሚል መሆኑንም አመልክተዋል።


በተለይ ባለፉት ሶስት ቀናት ወደ አካባቢው እየተመላለሰ ያለው አካል ነዋሪውን በገዛ ቤቱ ሰላም ነስቶታል ሲሉም ይናገራሉ።


አንዳንዶቹ ደግሞ በአካባቢው ወዳለው አስተዳደር ሔደው አቤት ለማለት ሲሞክሩ የተሰጣቸው ምላሽ ተነሱ ከተባላችሁ ተነሱ ነው በቃ የሚል አምባገነናዊ ምላሽ ነው ይላሉ።


ከዛም አልፎ እንደባለንብረትነታቸውና እንደባለመብት ያማከራቸውም ሆነ ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንዲያውቁ ለማድረግ የሞከራ አንዳችም አካል እንደሌለ ይናገራሉ።


ከጋራ መኖሪያ ቤቱ ባለንብረቶች አብዛኞቹ ደግሞ የሚጠበቅባቸውን እዳ ከፍለው የጨረሱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።


ነገር ግን ሁሉንም ካልዋጥኩ የሚለው ሰው በላው ስርአት ግን በህጋዊ መንገድ የተሰራውንና በቀድሞ ስርአት የተገነባውን ይሄንን ህንጻ ለማፍረስ ጫፍ ላይ ደርሷል ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page