በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት መስሪያ ቤት አጥርን ያስፈረሰው አብይ አህመድ የተሰጠውን ከባድ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ድንጋጤ ውስጥ መግባቱን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገልጹ።
የንጹሃንን ቤት በማፍረስ ህዝብን እያስለቀሰ ያለው አብይ አህመድ ከቤተ መንግስት አዲስ አበባን ልቃኝ ብሎ መውጣቱን ይናገራሉ።
እናም ወደ መስቀል አደባባይ ሲያቀና የተባበሩት መንግስታት ለደንነት በሚል ከፍ አድርጎ በከፍተኛ ወጭ ያስገነባውን የህንጻ አጥር መመልከቱን ገልጸዋል።
ነገር ግን የተገነባን በማፍረስ ነፍሱን የሚያስደስተው ግለሰብ በፍጥነት ይህ አጥር ይፍረስ የሚል ትእዛዝ ማውረዱንና ወዲያው በአፍራሾች ፍርስርሱ እንዲወጣ ማድረጉን የውስጥ ምንጮቹ ይናገራሉ።
ይህንን ህገወጥ ተግባር ይመለከት የነበረው የተቋሙ ሰራተኛም በምስል የሚደረገን ነገር ሁሉ ቀርጾ ይይዝና ለተባበሩት መንግስታት ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረጉን አስታውቀዋል።
የሚመለከተው አካልም ንዴት በተሞላበት በሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እውቅና ተሰጦት የተሰራ የደንነት አጥር ለምን ይፈርሳል በሚል ከባድ ቁጣ ማስነሳቱን የውስጥ ምንጮቹ ይናገራሉ።
በዚህ የተደናገጠውና የሚይዘው ያጣው አብይ አህመድ አጥሩ የፈረሰው በስህተት ነው ብሎ ለማሳመን መከራውን ሲያይ መክረሙን ገልጸዋል።
ለአጥሩ ግንባታ እስከ 6ሚሊየን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል የሚሉት የውስጥ ምንጮቹ ይሄንን ኪሳራ ያመጣው ግለሰብም በድጋሚ አጥሩን ለማሰራት መከራውን እያየ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።