top of page

(ኢትዮ 360-ሐምሌ 4/2015)የሸዋ ሮቢት ከተማ ሕዝብ የኦህዴዱን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች አሳፍሮ መለሰ።


የሸዋ ሮቢት ከተማ ሕዝብ በሰው በላው ስርአት መሪ አቢይ አሕመድ ለስብሰባ የተላኩ ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችን አሳፍሮ መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።


ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች የሸዋ ሮቢት ከተማን ሕዝብ ትላንት ሰብስበው እንደነበር ምንጮቹ ይናገራሉ።

የጦር ጄኔራሎቹ የጠሩት ስብሰባ ዋና አላማም እኛ ሰላም እንፈልጋለን ፋኖዎችም ይሄን አውቀው በሰላም ወደየቤታቸው ይግቡ በሚል ለማግባባት እንደነበር ገልጸዋል።


በስብሰባው የተገኘው የሸዋ ሮቢት ከተማ ሕዝብ ግን ያላወቃችሁት ነገር እኛም ፋኖ መሆናችንን ነው፣እኛ ፋኖች ደግሞ ሰላምን እያወክን አይደለም፣ሰላማችንን እይወካችሁት ያላችሁት እናንተ ናችሁ በሚል እቅጩን ነግሯቸዋል ይላሉ።


እናንተ ልጆቻችሁን በሠላም ታስተምራላችሁ በንግዱም በየመሥሪያ ቤቱም የናንተ ወገኖች እንደልብ ይሆናሉ፣ የእኛ ልጆች ግን መስራትም መማርም እንዳይችሉ ሆነዋል ሲሉ ነዋሪዎቹ በስብሰባው ላይ ተናገረዋል።


በአካባቢው ንግድ ሱቆች የተዘጉትም ሆነ የባጃጅ አገልግሎት የቆመው በናንተ ምክንያት ነው ስለዚህ ሰላም ከፈለጋችሁ በአስቸኳይ ሸዋ ሮቢትን ለቃችሁ ውጡልን ሲል ህዝቡ ማስጠንቀቂያውን በግልጽ ሰቷቸዋል ብለዋል።


በስብሰባ ህዝቡን ማሳመን ያልተሳካለት የጄኔራሎች ስብስብ የኦህዴዱን መከላከያ እየመራ በአካባቢው ወደሚገኘው ካምፕ ማስገባቱን ይናገራሉ።


ትላንት በተደረገው ስብሰባ ያልተሳካለትና የህዝቡ ምላሽ ያስደነገጠው የኦህዴዱ ስብስብ 12 ሰአት አድርጎት የነበረው የሰአት እላፊ ወደ 2 ሰአት የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጆች እንቅስቃሴ ደግሞ እስከ 12 ሰአት ሆኖ እንዲውል አድርጓል ብለዋል።


እንዳይሰሩ ታግደው የነበሩት ባጃጆችም ሙሉ ቁጥርና ጎዶሎ ቁጥር በሚል በፈረቃ ከዛሬ ጀምሮ እንዲሰሩ መወሰኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል።


ሰሞኑን መንገድ በመዝጋትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ጭምር ህብረተሰቡን አላንቀሳቅስ ብሎ የነበረው የኦህዴዱ ሃይል በአንድ ጊዜ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱ ሌላ አጀንዳ ሊኖረው ይችላል ሲሉም ምንጮቹ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።


በጀግንነቱ ምንም የማይወጣለት የሸዋ ሮቢት ህዝብ አቋሙን በግልጽ ማስቀመጡን ተከትሎ ነገሮችን ለማስተካከል ሞክሬያለሁ የሚለውን ይሄንን የገዳዮች ስብስብ ህብረተሰቡ በአይነ ቁራኛ እየተከታተለው መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በጥንካሬው መብቱን ማስከበር ቢችልም የገዳዩ ቡድን ስብስብ ግን ያቀደው ሌላ አጀንዳ መኖሩ በግልጽ ስለሚታወቅ አሁንም ህዝቡ በተጠንቀቅ ሆኖ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በዛው በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ አካባቢ መሳሪያ ይዘው ጠፍተዋል በሚል የሚሊሻ አባላት ቤተሰቦች በብአዴኑ ስብስብ እየተሰቃዩ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጸዋል።


በቤተሰቦቻቸው ላይ ይሄንን ስቃይ እያደረሱ ያሉት ደግሞ የራሳችን ወገኖች የሚሏቸው የብአዴኑ ሆድ አደር የፖሊስና የሚሊሻ አባላት መሆናችውን አመልክተዋል።


የሚያሳዝነው ይላሉ ምንጮቹ በዚህ ማሰቃየት ውስጥ ደግሞ ምንም የማያውቁ ህጻናት ላይ ከባድ ድብድባና እንግልት እየደረሰ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page