top of page

(ኢትዮ 360-ሐምሌ4/2015)በደንቢዶሎ መቻራና አካባቢው የኦነግ ቡድን የአማራ ተወላጆችን ገደለ።


በቄለም ወለጋ ደንቢዶሎ ዞን የመቻራ ከተማንና አካባቢውን ለሊቱን የወረረው የኦነግ ገዳይ ቡድን በከፈተው ተኩስ ቁጥራቸው የማይታወቅ የአማራ ተወላጆችን መግደሉን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


እስካሁ በሺዎች የሚቆጠሩና ከየአካባቢው የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የሚኖሩባትን የመቻራ ከተማን ደፎር የማያውቀው ገዳይ ቡድን ዛሬ ለሊቱን አካባቢውን ወሮ ማደሩን ያናገራሉ።


የመጣው ገዳይ ቡድን ከፍተኛ ቁጥር እንደነበረው የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ወደ ከተማዋ ዘልቆ በመግባትም የአማራ ተወላጆችን ከመግደል አልፎ ባንኮችን፣ሞባይል ቤቶችንና የተለያዩ የንግድ መደብሮችን መዝረፉን ገልጸዋል።


ከዚህ በፊት በቄለም ወለጋ ደምቢዶሎ በሚገኙትና የአማራ ተወላጆች መኖርያ በሆኑት መንደሮች ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ሲገል የቆየው ይሄ ስብስብ ዛሬ ለሊቱን እስከ ከተማ ዘልቆ ሲገባ በ10 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የብርሃኑ ጁላ ጦር ቆሞ ይመለከት ነበር ብለዋል ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ።


ይሄ ስብስብ የሚገለውን ገሎ የሚዘርፈውን ዘርፎ ሲጨርስ ግን ተባባሪ የሆነው የብርሃኑ ጁላ ጦር ወደ አካባቢው መግባቱን ተናግረዋል።


ይሄው የገዳዮች ስብስብ በከተማ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ሃይሉን እስከ ገጠሩ ድረስ እንዲገባ ማድረጉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በአካባቢው የኢንተርኔት አገልግሎት ብዙም እንዳይኖር ከመደረጉ ጋር ተያይዞም በገጠሩ አካባቢ ይሄው ገዳይ ቡድን ያደረሰውን ጉዳት ማወቅ አልተቻለም ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page