(ኢትዮ 360 - መስከረም 15/2016) በደቡብ ወሎ የአምባሰል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት በህዝባዊ ሃይሉ ተሰበረ።
- Ethio 360 Media 2
- Sep 26, 2023
- 1 min read
(ኢትዮ 360 - መስከረም 15/2016) በደቡብ ወሎ የአምባሰል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት በህዝባዊ ሃይሉ ተሰበረ።
በደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ የሚገኘው የአምባሰል ወረዳ ፖሊሲ ጽህፈት በህዝባዊ ሃይሉ መሰበሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ጽህፈት ቤቱን ለማዳን ሲንፈራፈሩ የነበሩ የሆድ አደሩ ብአዴን አድማ ብተናና ሚሊሻ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከጥፋታቸው ያልታረሙና ከጠላት ቡድን ጋር በመሆን አሁንም ወገኖቻቸውን በመውጋት ላይ ላሉት የባንዳ ስብስቦችን ህዝባዊ ሃይሉ በተለያዩ መንገዶች ለማስመከር ቢሞርክም ሊሰሙ ባለመቻላቸው ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ቀጥሏል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ህዝባዊ ሃይል በዚህ ደረጃ የህልውና ዘመቻ እያደረገ ባለበት ሰዠት አገው በሚል የተሰባሰበ ቡድን ደግሞ አገው ክልልን እመሰርታለሁ በሚል መከራውን እያየ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ሰሞኑን ኢትዮ 360 ባወጣው መረጃ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሰለጠነውን ሃይል ሲያስመርቅ እንደነበር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
በነአበባው ታደሰና ሰማ ጥሩነህ የሚመራው ይሄ ስብስብ አሁን ደግሞ ክልል እመሰርታለሁ ብሎ ብቅ ማለቱንም ምንጮቹ ተናግረዋል።