በጎንደር አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሊደፍራት የሞከረውን የገዳይ ቡድን አባል በድንጋይ በመምታት ብቻ ጥቁር ክላሽ መሳሪያ ስትማርክ ህዝባዊ ሃይሉ ደግሞ በተለያዩ አካባቢዎች በወሰደው ርምጃ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ማክሰኝት አካባቢ ገዳይ ቡድኑ ይንቀሳቀስ የነበረበት አካባቢው ውሃ ለመቅዳት በመሄድ ላይ ያለችን አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪን ለመድፈር መሞከሩን ይናገራሉ።
ተማሪዋም ያለምንም ትግል በድንጋይ ብቻ ክላሽ መሳሪያውን ማርካ በእጇ ማስገባት ችላለች ሲሉም አባላቱ ተናግረዋል።
ከዚህም ሌላ ዛሬ በተለያዩ አቅጣጫዎች ያለው ህዝባዊ ሃይሉ ስብስብ በጋራ ማክሰኝት ላይ ለሊቱን ጥቃት መፈጸሙን ይናገራሉ።
በዚህም የገዳዩ ቡድንና አድማ ብተና በሚል በተሰባሰበውን ሆድ አደር ሙስትና ቁስለኛ አድርጎታል ብለዋል።
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን መከለያ አድርጎና ህዝባዊ ሃይሉን ትደግፋላችሁ በሚል በየፖሊስ ጣቢያዎች የታሰሩ ወጣቶችን ሙሉ በሙሉ ነጻ ሲያወታ ፖሊስ ጣቢያዎቹም ከዚሁ ቡድን መላቀቃቸውን ይናገራሉ።
ቆላ ድባ ላይም በተመሳሳይ ከፍተኛ ውጊያ ሲደረግ ቆይቶ ገዳይ ቡድን ማጽዳት ብቻ ሳይሆን በግፍ የታሰሩ ወገኖቻቸውንም ነጻ ማውጣታቸውን ነው ያመለከቱት።
የአድማ ብተናውን ለማምጣት በሚል ሁለት ፓትሮል ሙሉ የገዳይ ቡድኑ አባላት ደረስኬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ገና ያሰበው ቦታ ሳይደርስ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን መደረጉንም አንስተዋል።
ከተገደለውና ከተማረከው ውጮ ወደ አዘዞ የፈረጠጠም መኖሩን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ህዝባዊ ሃይሉ በዚህ መልኩ የህልውና ትግሉን ሲያካሂድ ገዳይ ቡድኑ ደግሞ በንጹሃን ላይ የሚፈጽመውን ጥቃት ቀጥሎበታል ብለዋል።
መታወቂያ አላሳያችሁም በሚል ሁለት ወጣቶችን በአደባባይ የገደለው ቡድን በቀበሌ 18 የሚገኘውን የኢትዮ ቴሌ መስሪያ ቤትን ባዶ እስኪሆን መዝረፉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።