የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በአል በሃገር ውስጥና በውጭ በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርአት በመከበር ላይ ነው።
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የእምነቱ አባቶችና ምዕመናን በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት እየተከበረ ያለው ይሄው በአላ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎችም ፍጹም ሃይማኖታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ እየተከበረ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በየትም አካባቢ እንዳይውለበለብ ለማድረግ ሲለፋ የነበረው የሰው በላው ስብስብ ያሰበውን ያህል እቅዱን ሊያሳካ አልቻለም ሲሉም ተናግረዋል።
በፍጹም ሃይማኖታዊ ጨዋነቱ የሚታወቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናንም ባህላዊ አላባሳትን በመልበስ ለበአሉ ትልቅ ግርማ ሞገስን ሰተውታል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጅድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች በመከበር ላይ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች አስታውቀዋል።
የመውሊድ በዓል የነቢዩ መሐመድ መልካም ተግባራትን በማሰብና የተለያዩ ሃይማኖቱ የሚፈቅደውን ተግባር በመፈጸም የሚከበር በአል መሆኑንም አስታውሰዋል።