top of page

(ኢትዮ 360-ሰኔ 14/2015)በቀብሪ ደሃር ከተማ ከመከላከያ ካምፕ አምልጦ የወጣ አንድ የኦህዴዱ ሰራዊት አባል አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ገደለ።


በሶማሌ ክልል ቀብሪ ደሃር ከተማ ከመከላከያ ካምፕ አምልጦ የወጣ አንድ የኦህዴዱ ሰራዊት አባል በከፈተው ተኩስ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ሲገድም ሶስት ያህል ሰዎችን ማቁሰሉን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


ወደ አካባቢው የኦህዴዱ መከላከያ መግባቱ አስቀድሞም ቢሆን በህበረተሰቡ በኩል ተቀባይነት አላገኘም ይላሉ።


ትላንት ምሳ ሰአት አካባቢ በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባላገኘውና ከካምፑ አምልጦ በወጣ አንድ አባል አራትን ንጹሃን ተገለዋል ሶስት፣ ያህል ቆስለዋል ብለዋል።


ህብረተሰቡ ላይ ለመተኮስ የሚያደርስ አንዳችም የተፈጠረ ነገር የለም ሲሉ ሁኔታውን ይገልጻሉ።


በድንገት ተኩስ የተከፈተበት ህዝብም ያለውን ነገር ሁሉ ይዞ ወቶ ለሊቱን ሙሉ ሲቃወም ማደሩን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 አስታውቀዋል።


ለሰራዊቱ አባላት ከካምፕ አምልጦ ይሄን ጥቃት ለማድረስ ዋናው ምክንያት ደግሞ የሰራዊቱ አባላት መጥፋት ያስደነገጠው አካል የሰጠው ትእዛዝ ነው ይላሉ።


ትላንትም ከካምፕ ያመለጠውና በአካባቢው ሚሊሻና ማህበረሰብ እንዲቆም በመደረጉ ተኩስ ከፍቷል ብለዋል።


ህብረተሰቡ አሁንም የመከላከያ ሃይል የሚባል ይውጣ በሚል በያዘው አቋሙ ቀጥሏል ይላሉ።


አሁንም በአካባቢው ካለው ሁኔታ አንጻው የማህበረሰቡ ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page