በአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር በሚል የተቋቋመው የዘረፋ ክፍል አሁን ደግሞ በግብር ምክንያት የሚንገላታዉን ህዝብ ኦሮምኛ ተናጋሪ ካልሆነ የቅድሚያ ተስተናጋጅ አይሆንም የሚል መመሪያ መውረዱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ግብር ለመክፈል የሔደ የከተማዋ ነዋሪ በመጀመሪያ ፋይሉን እንዲያቀርብ ይጠየቃል ይላሉ።
ይዞ የቀረበውን ፋይል ከተቀበሉ በኋላም የቀጠሮ ቀን ይሰጠዉና በዚህ ቀን ተመለስ እንደሚባልም ምንጮቹ ተናግረዋል።
ነገር ግን ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ሲሔድ የሚሰጠው ምላሽ ፋይሉ የለም ጠፍቷል፣ ለመፈለግ ደግሞ 200,000 ብር አምጣ የሚል ጥያቄ እንደሚቀርብለት ገልጸዋል።
ክፈል የተባለው ነዋሪ አቤት ቢልም የሚሰማው የለም፣ስለዚህ የተጠየቀውን ብር መክፈል ግዴታውን ይሆናል ይላሉ።
ነገር ግን አልከፍልም ብሏል በሚል ለተፈረጀው ደግሞ የሚጠበቀው ሰኔ 30 እስኪደርስ ብቻ ነው ብለዋል።
ምክንያቱም ከሰኔ 30 በሁዋላ ግብር አልከፈለም በሚል ቤቱን ለመውረስ በመዘጋጀታቸው ነው ሲሉ እውነታውን አስቀምጠዋል።
ይሄ ሁሉ እንግልትና በደል እየደረሰበት ያለው ደግሞ ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆነው የህብረተሰብ ክፍል ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።