በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቦሌ መድሃኒአለም ካቴድራል ገዳም ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ ማመናኑ ለኢትዮ 360 አስታወቁ።
የቦሌ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ቤተክህነቱ ባወገዘው ህወገወጥ ቡድን በመወረሩ የቤተክርስቲያኑ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል ይላሉ፣
አዲስ ተመርሶ ወደ ቤተክርስቲያኗ የመጣው አካል ሰንበት ትምህርት ቤቱን ሁሉ ለሁለት በመክፈል ጭምር ቤተክርስቲያኑን አደጋ ላይ መጣል ብቻ ሳይሆን ለቤተክርስቲያኗ ስለእውነት የቆሙ ወጣቶችን ሁሉ እስከማሳሰር የደረሰ ነው ይላሉ።
ይሄው የህገወጥ ስብስብ ስለቤተክርስቲያኗ የቆሙና እውነተኛ አገልጋይ የሆኑ ካህናትን ለማባረር ደብዳቤ እስከማውጣት ደርሷል ብለዋል።
ለቤተክርስቲያኑ የጀርባ አጥንት የሚባሉት ካህናትን ከወጣቶች ጋር ተባብራችኋል በሚል ብቻ ለማራረ የተነሳው ህገወጥ ቡድን ዋናውን ስራ የሚሰራው ከነአቡነ ሔኖክ ጋር በመሆን ነው ሲሉ ምእመናኑ ይናገራሉ።
የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ወደ ግል ባንካቸው ለማስገባት ያደረገው ሙከራ ያልተሳካለት ይሄው ስብስብ የእምነት ቦታውን የፖለቲካ መንደር አድርጎታል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።