(ኢትዮ 360-ሰኔ 14/2015)የታገቱትን የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎችን ለማስፈታት ለእያንዳንዱ አንድ ሚሊየን ብር ተጠየቀ።
- Ethio 360 Media 2
- Jun 21, 2023
- 1 min read
በኦሮሚያ ክልል አሊ ዴሮ አካባቢ የታገቱትን የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎችን ለማስፈታት ለእያንዳንዱ አንድ ሚሊየን ብር መጠየቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ምንም ማድረግ አልቻልንም የሚሉት ቤተሰቦቻቸው ገንዘቡን ሰተው ወገኖቻቸውን በህይወት ለማስመለስ እየሞከሩ መሆኑን ይናገራሉ።
አሽከርካሪዎቹ ብቻ ቁጥራቸው ወደ 34 ይደርሳል የሚሉት ቤተሰቦቻቸው ከነሱም በተጨማሪ ሌሎች ተሳፋሪዎችን ጨምሮ ከ60 በላይ እንደሚሆኑም ይናገራሉ።
ለዚህ ሁሉ ታጋች ደግሞ እንደ ሰው ታይተው ሳይሆን እንደ ከብት መደብ ዋና ይወጣለታል ሲሉ በሃዘኔታ ይገልጻሉ።
ይሄንን ብር ለመክፈል ደግሞ አማራው ቤቱንም ሆነ ያለውን ከብቱን በመሸጥና ወገኑን ለማዳን እየጣረ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።