(ኢትዮ 360-ሰኔ 21/2015)አንድ ከፍተኛ የአፍሪከ ዲፕሎማት በኦነግ ታገቱ።
- Ethio 360 Media 2
- Jun 28, 2023
- 1 min read
አንድ ከፍተኛ የአፍሪከ ዲፕሎማት በኦነግ ገዳይ ቡድን መታገታቸውም የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።
በከፍተኛ ሚስጥር እንዲያዝ የተደረገውን ይሄውንን ጉዳይ በዋናነት ውስጥ ለውስጥ በሚስጥር ለመጨረስ እየሰሩ ያሉት ደግሞ የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ቢሮው የውጭ መምሪያ ክፍሎች መሆናቸውን ይናገራሉ።
የየትኛው የአፍሪካ ሃገር ዲፕሎማት እንደሆኑ ማወቅ ያልተቻለውን ግለሰብ ለማስለቀቅ ደግሞ የኦነጉ ቡድን ከፍተኛ የዶላር መጠን መጠየቁን አመልክተዋል።
አዲስ አበባ አካባቢው ለስራ ከሔዱበት ወደ ኤምባሲያቸው ሲመለሱ የታገቱት አፍሪካ ሃገር ዲፕሎማት እገታ ጋር በተያያዘ ቤተመንግስቱን የተቆጣጠረው አካል እጁ ኣይኖርበት አልቀረም ሲሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ከአንድ ቀን በፊት የታገቱትን ዲፕሎማት ለማስለቀቅ ብር ሳይሆን ከፍተኛ የዶላር መጠን የጠየቀው ይሄው የገዳዮች ስብስብ ሰሞኑን አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲና ሃና ማሪያም አካባቢው መታየቱን ኢትዮ 360 በመረጃው ማውጣቱን ያስታውሳሉ።
እስካሁን ድረስ ስለዲፕሎማቱ እገታ ከኤምባሲውም ይሁን ኢትዮጵያን አስተዳድራለሁ ከሚለው አካል አንዳችም የወጣ መረጃ እንዳይኖር ለማድርግ በከፍተኛ ጥንቃቄና ሚስጥር እየተሰራ መሆኑንም የውስጥ ምንጮቹ ይናገራሉ።