በኢትዮጵያ በሚገኙ የግል ባንኮች ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የተከሰተው ሁሉም የግል ባንኮች ከ5 ቢሊዮን ያላነሰ ጥሬ ገንዘብ በመሰብሰብ ትግራይ ክልል ወደአሉ ቅርንጫፎች እንዲልኩ በመደረጉ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አስታወቁ።
ይሄ የተደረገው ደግሞ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተደረገ በተባለ ማግስት መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከዚህ ጋር ተያያዞ ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የግል ባንኮች ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከደንበኞቻቸው ጋር ዱላ ቀረሽ ንትርክ እና ጭቅጭቅ ውስጥ መግባታቸውንም ያነሳሉ።
ሰራተኛው ይሄ ነገር ከአቅሙ በላይ ስለሆነ የዚህ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ምን እንደሆነ የበላይ ሃላፊዎችን በማነጋገር ጭምር ለማጣራት ከፍተኛ ትግል እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።
እንደእውነቱ ከሆነ ይላሉ ምንጮቹ ብሩ ትግራይ ክልልም ቢሆን የሄደው ገንዘቡ ወደ ባንክ ቀጥታ ከሆነ የገባው ከባንክ ስርዓት ስላልወጣ የገንዘብ እጥረቱ አይፈጠርም ነበር ሲሉም ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ።
ከዚህ በመነሳትም የግል ባንኮቹ ወደ ትግራይ ላኩ የተባለው በቢሊየን የሚቆጠር ብር አንድም መንግስት ነኝ የሚለው አካል አላከውም ካልሆነም እዛ ከደረሰ በኋላ ወደ ባንክ እንዳይገባ ተደርጓል ማለት ሲሉም ምንጮቹ እየተሰራ ያለውን ስርአታዊ ወንጀል ያጋልጣሉ።
የግን ባንኮቹ አሁን ላይ ለግለሰብም ሆነ ለድርጅቶች የሚሰጡት የገንዘብ አቅም በየቀኑ እየቀነሰና የለም ወደሚባል ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።