ከሁለት ቀን በፊት ይላሉ ለዚሁ ገዳይ ቡድን ያደረው የክልሉ ሚሊሻ በጣለው ቦንብ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ላይ ጉዳት አድርሶ እንደነበር ይናገራሉ።
ነገር ግን ይሄንን ግድያ ተጠቅሞ የኦህዴዱ ሃይል ወደ ከተማ ለማለፍ ያደረገው ሙከራ በህዝባዊ ሃይሉ ከሽፎበታል፣ጀማ ላይ ማረፊያ አድርጎት የነበረውን ካምፕም ከጥቅም ውጪ አድርጎታል ከ2ሺ በላይ የኦህዴዱ ሃይልም ተገሏል ብለዋል።
ህዝባዊ ሃይሉ ሙትና ቁስለኛ ካደረጋቸውም ሌላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል ማርኳል፣የግልና የቡድን መሳሪያዎችንም ማርኳል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ደብረብርሃን ላይ የሚንቀሳቀሰው ሃይል ደግሞ መንገድ በመዝጋት ጭምር በአካባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ማድረጉንም ተናግረዋል።
ይሄ ደግሞ ደብረብርሃን ላይ ያለን ሃይል ለማዛወር ቢሆንም አይሳካላትም ሲሉ እውነቱን ተናግረዋል።
ደብረብርሃን ላይ ከሶማሊያ አምጥቶ ያፈሰሰው የኦህዴድ ሃይል ደግሞ በኮሌራ ወረርሽኝ ተይዞ ሁለት ሆስፒታሎችን ሞልቷል ሲሉ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ይናገራሉ።
አባላቱ ከህመሙ የተነሳ በእግራቸው መንቀሳቀስ በማይችሉበት ሁኔታ መታመማቸው ነው ለኢትዮ 360 የገለጹት።