በጉራጌ ዞን በአበሽጌ ወረዳ የአማራ ተወላጅ የሆኑ አመራሮች፣ባለሃብቶች፣አርሶ አደሮችና ወጣቶች በተለየ መልኩ እየታፈኑ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ወረዳዋ ለኦሮሚያ ክልል ቅርብ ናት የሚሉት ነዋሪዎቹ በአካባቢው ደግሞ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው ነዋሪ ደግሞ የአማራ ተወላጅ ነው ይላሉ።
ማህብረሰቡን ያስተባብራሉ ተብለው የሚታሰቡ አመራሮችም ሆኑ ወጣቶች ብሎም ተማሪዎች ሁሉ እየተለቀሙ ወዳልታወቀ ቦታ እየተወሰዱ ነው ብለዋል።
ሰሞኑን በተለየ መልኩ የተጀመረው አፈና የጉራጌ ህዝብ እያነሳ ካለው የክልልነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል።
የአሁኑ አፈና ዋና ትኩረቱ አማራ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።