ከሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ታፍነው በየእስር ቤቱ የታጎሩ የአማራ ተወላጆችን ለመረሸን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አስታወቁ።
በየማጎሪያ ቤቱ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ በተከታታይ የግድያ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ማድረስ እንደልማድ ተደርጎ የተወሰደ ነው ይላሉ የውስጥ ምንጮቹ።
የግፍ ታሳሪዎቹን መፀዳጃ ቤት ውስጥ ማጎር እና መመገቢያም መኝታም በጣም ከሚከረፋ ሽንት ቤት ውስጥ እንዲሆን ማድረግ ደግሞ ሌላኛው የማሰቃያ መንገድ ነው ይላሉ።
እንደማሳያም ቂሊጦ ከሚባለው ማጎሪያ ያሉ የግፍ እስረኞችን የነበሩበትን በጣም ጠባብ ክፍል ቀለም ልንቀባላችሁ ነው በማለት እዲወጡ ካደረጓቸው በኋላ ለአንድ ሳምንት ሽንት ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገዋል ሲሉም እየደረሰ ያለውን ግፍ ያሳያሉ።
ግፉን መቻል ያቃታቸው እስረኞችም ወደ ክፍላችን መልሱን በሚል ብቻ ላቀረቡት ጥያቄ ዱላ እና መሳሪያ የያዘ ኮማዶ ተልኮ ከፍተኛ የሆነ የግድያ ማስፈራሪያ እና ሙከራ እንዲደረግባቸው ሆኗል ብለዋል።
የውስጥ ምንጮቹ እንደሚሉት በየማጎሪያው ስፍራ እየተደረገ ያለው ዝግጅት በግፍ የታሰሩ የአማራ ተወላጆችን ለመረሸን ያለመ ነው።
ሌላው አሳፋሪና አሳዛኙ ነገር ደግሞ ከታሰሪዎች መካከል ግብረ-ሰዶም ወይም በወንድ የተደፈሩ ወንድሞች መኖሩ ነው ይላሉ።
የተወሰኑት ላይ ደግሞ በአፋቸው ሽንት የተሸናባቸው እና ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከዚህ ጋር ተያይዞም አብዛኞቹ የግፍ እስረኞች ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም አጃቢ ፖሊስም ሆነ የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ የሆነ የዘር ጥላቻ ያለባቸው የፋሺሽቱ አገልጋዮችና ዘረኞች በመሆናቸው አግባብ ያለው ህክምና ማግኘት አልቻሉም ሲሉም እውነቱን ያስቀምጣሉ።
. በየማረሚያ ቤቱ በተለይም የግፍ እስረኞቹ የታጎሩበት ዞን ከጥበቃ ጀምሮ ያሉት በጠቅላላ የአንድ ብሔር ተወላጅ ከመሆናቸው በላይ ከፍተኛ የሆነ የዘር ጥላቻ ያለባቸው መሆኑ ሌላ መከራ ነው ብለዋል የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች።
በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ህዝባዊ ሃይሉ ሽንፈትን ባከናነባቸው ቁጥር እልሃቸውን የሚወጡት በዚሁ የግፍ እስረኛ ላይ ነው ይላሉ።
በተለየ መልኩ ደግሞ በዶ/ር ወንደሰን ላይ በየለቱ የሚደርሰው የእንገልሃለን ዛቻው በየእለቱ እየከፋ መቷል ብለዋል የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች።
Comments