የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች መኖሪያ መንደር ተሰብሮ 6 የፋብሪካው ሰራተኞች በገዳዩ ቡድን ከየቤታቸው ታፍነው መወሰዳቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ከለሊቱ ስድስት ሰአት ቤታቸው ሰብሮ አፍኖ የወሰዳቸው ገዳይ ቡድን በአንድ ሰው 500 ሺህ ብር መጠየቁንም ምንጮቹ አመልክተዋል።
ሰኞ ለሊት ታፍነው የተወሰዱት እነዚህ ሰራተኞች ወዴት ታፍነው እንደተወሰዱና በህይወት ስለመኖራቸው ባልታወቀበት ሁኔታ ይሄንን ያህል ብር የተጠየቁት ቤተሰቦቻቸው በእንባ ከመራጨት ውጪ ማድረግ የቻሉት አንዳችም ነገር የለም ብለዋል ምንጮቹ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በአዲስ አበባ በቡራዩ አካባቢው ከየቦታው ታፍነው የተወሰዱ ከ500 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች በአንድ ቦታ ታጎረው በረሃብና በውሃ ጥም እንዲያልቁ እየተደረገ ነው ሲሉ ምንጮች አመልክተዋል።
ከዛም አልፎ በንጹሃን የግፍ ታሳሪዎች ላይ የሚፈጸመው ድብደባና ማስፈራሪያም ከቀን ወደቀን እየከፋ መቷል ብለዋል የኢትዮ 360 ምንጮች።
በየማጎሪያው ንጹሃን ዜጎችን እያጋዛ ያለው የሰው በላው ስርአት እስካሁን የታፈነው ሰው በቂ አይደለም የሚል ግምገማ በማስቀመጥ የአማራ ተወላጆችን ጨምሮ የደቡብና የአዲስ አበባ ወጣቶችን በገፍ ማፈሱን መቀጠሉንም
Komentarze