(ኢትዮ 360 - ነሀሴ 4/2015) በደቡብ ክልል በአርባምንጭና በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የተጀመሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሰው በላው ሃይል ታፈኑ።
በደቡብ ክልል በአርባምንጭና በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የተጀመሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሰው በላው ሃይል መታፈናቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ገዳይ ቡድኑን በክልሉ የህዝባ ተቃውሞ ተነስቶባቸዋል የተባሉ አካባቢዎች ላይ ያሰማራው ገዳዩ ስርአት በህዝባዊ አመጹ ውስጥ ዋና አስተባባሪ ናቸው የሚባሉ ወጣቶችን በገፍ እያፈነ መሆኑንም ያነገራሉ።
በዚህ መሃልም በድብደባ የተጎዱ ወጣቶች መኖራቸውን ነው ምንጮቹ የሚናገሩት።
ዛሬ በአርባምንጭ ሊካሄድ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞም በዚሁ ሃይል መታፈኑን ጠቁመዋል።
ድምጹን እንዳያሰማ የታፈነው ማህበረሰብም በቤት ውስጥ አድማውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ሳይናገሩ አላለፉም።
የጋሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላትም በዚሁ ቡድን እየተሳደዱና እየታፈኑ መሆናቸውንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።