በ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና በወሰዱ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊጋለጥ የገባል ሲሉ የኢትዮ ምንጮች ገለጸዋል።
ወንዶች በከባድ ተደብድበዋል፣ሴቶች ተደፍረዋል፣ በፍተሻ ሰበብ ቤተሰብ የሰጣቸው ገንዘብ ሰው በላው ስርአት ባሰማራው ሃይል እንዲሰርቁ ተደርገዋል ይላሉ።
ኢትዮ 360 በቅርቡ ባወጣው መረጃም የተረጃ ልጆች በሚል ተለይተው እንዲፈተኑ ለተደረጉት ተማሪዎች አንድ አስተማሪ ተመድቦ ለጥያቄዎቹ መልስ ሲሰጥ መቆየቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
በአንጻሩ ደግሞ ለብዙሃኑ ተማሪ ሶስት ፈታኞችን መድቦ የነበረው አካል በነዚሁ ተመደቡ በተባሉት መምህራን አማካኝነት ተማሪዎች እንዲፈሩ ሲደረጉ፣ሲረበሹ ሰአታቸውን ሳይጨርሱ ፈተና ሲነጠቁ መቆየታቸውንም ኢትዮ 360 በመረጃዊ ሲያጋልጥ ቆይቷል።
በቃሊቲ አካባቢ ለፈተና የተመደቡ ተማሪዎች ላይ የደረሰው ግን ሊናገሩትና ሊሰሙት የሚከብድ ነው ሲሉም ምንጮቹ ይናገራሉ።
በቅርቡ ኢትዮ 360 ያናገራቸው የተፈታኝ ተማሪዎች ወላጆች ይሄንን ግፍ የፈጸመው ብርሃኑ ነጋ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይቅረብልን ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል።