በናዝሬትና አካባቢው የገዳዩ ቡድን ስብስቦች ተሽከርካሪ በማስቆም የአማራ ተወላጅ የሆኑ አሽከርካሪዎችን እያፈኑ መሆኑ ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 አስታወቁ፣
አሽከርካሪዎቹ አማራ መሆናቸው የሚለየው ደግሞ መንጃ ፈቃዳቸውን በማየት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።
የሚገርመው ይላሉ ምንጃ ፈቃዱ አማራ ነው የሚል ከሆነ በቀጥታ ወደ ማፈኛ የሚወሰደው አሽከርካሪው ብቻ ሳይሆን ያሳፈረውም መንገደኛ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ዛሬ በአካባቢው በብዛት ወደ ማፈኛ የተወሰዱት ደግሞ ከደብረብርሃን አካባቢው የመጡ አሽከርካሪዎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ሌላው አሳዛኝ ነገር ግን ከአሽከርካሪው የሚነጠቀው መንጃ ፈቃድ በዚሁ ጨካኝ ቡድን ተሰባብሮ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን መደረጉ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ በመረጃቸው ላይ አስታውቀዋል።