top of page

(ኢትዮ 360 -ነሐሴ 4/2015) በጎጃም ብቸናና አካባቢው የገዳዩ ስርአት ሃይል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ከፈተ።


በጎጃም ብቸናና አካባቢው የገዳዩ ስርአት ሃይል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት መክፈቱን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


ወደ 60 አውቶቡስና ወደ 40 ኦራል ተሽከርካሪዎች ሃይል ያስገባው አካል አርሶ አደሩን በግፍ እያስጨረሰው ነው ይላሉ።


በአካባቢው ያሉት የተመስገን ጥሩነህ ዘመዶች ደግሞ ንጹሃንን በማስገደል ተባባሪ እየሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።


ወደ ደብረወርቅና ሞጣ ለማለፍ እየሞከረ ያለውን ይሄንን ሃይል ሁሉም እንዲያግዘው ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


እስካሁን በተደረገው ትግልም በእነማይ ወረዳ ከየትመን እስከ ብቸና ያሉ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ባደረጉት ተጋድሎ 17ኦራል፣14 ድሽቃ፣32 ብሬን፣300በላይ ጥቁር ክላሽ እንዲሁም ሌሎች መሳሪያዎችን መማረካቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ይህ በእንዲህ እንዳለም ወደ ደብረብረሃን የገባው ገዳዩ ቡድን የነዋሪውን የእጅ ስልክና ብር እየዘረፈ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


ከደብረማርቆችስ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት በሉማሜ ከተማ በ6 ኤፌሳር የተጫነ ገዳይ ቡድን ወደ አካባቢው እየገባ መሆኑን ተናግረዋል።


የከተማውን ህዝብ እናሸብራለን በሚል ደግሞ ከተማው መሀል አስፓልት ላይ በፓትሮል ዲሽቃ በመያዝ ወደ ፊት እና ወደ ሁላ በማለት መሳሪያ እያወናጨፋ ህዝብን ሳይሆን ራሳቸውን ሲያሞኙ ውለዋል ሲሉም ሁኔታውን ያስቀምጣሉ።


በተያያዘ ዜና ሌሊቱን በሙሉ በደሴ ከተማ ወጣቶች በገፍ ሲታፈኑ ማደራቸውን ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።

በተጨማሪ ዛሬ ጠዋት ላይ የባጃጅና የሚኒባስ ሹፌሮችን በማስቆም የደብረ ብረሐን ና የደቡብ መንጃ የፍቃድ ያላቸውን ሲለቅሙ መዋላቸውን ምንጮቹ አመለክተዋል።


የከተማው ትራፊኮችን በሚል ቡድን ጠዋት በገላውዲዮስ መስመር የተጀመረው ነጠቃ ወደ ስላሴ ገንደ ሐራ መዞሩንና ከሰአት ደግሞ ከገንደ ጋራና ከዩኒቨርስቲ የሚመጡትንም በማስቆም መንጃ ፈቃዳቸውን እየነጠቁ መሆኑን ይናገራሉ።


ጠዋት ላይ በብዛት የአማራ ተወላጆችን መንጃ ፈቃድን እየነጠቀ ሲያፍን የዋለው ቡድን ከሰአት በኋላ ደግሞ የደቡብ መንጃ ፍቃድን የያዘን ሁሉ ሲለቅሙ መዋላቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


እንዲሁም በከተማው ከነሐሴው 4 ጀምሮ እስከ ነሀሴ 17 2015 ድረስ የባጃጅ እንቅስቃሴን ኮማንድ ፖስት ነኝ ብሎ ራሱን በሚጠራው አካል መታገዱን ይናገራሉ።


በእነማይ ወረዳ አስተዳደር ደግሞ አዲሱ ተሻለ የተባለ የብአዴን ሆድ አደር ለመከላከያ መረጃ እያቀበለ የእነማይን ህዝብ እያስፈጀ ነው ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page