top of page

ኢትዮ 360- ንቦት 30/2015) ማዳበሪያ በተለየ መልኩ ወደ ጅማና ወለጋ በገፍ እየተጋዘ ነው።


በኦሮሚያ ክልል ማዳበሪያ በተለየ መልኩ ወደ ጅማና ወለጋ በገፍ እየተጋዘ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


ይሄ ማዳበሪያ እየተጓጓዘ ያለው ደግሞ ገዳ የሚባለው የመጓጓዣ አገልግሎት ተመድቦለት መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ወደ ጅማና ወለጋ የእህል ማዳበሪያውን በገፍ እያጋዘ ያለው አካል የሸዋ ኦሮሞን ጨምሮ አማራና ደቡብን እስካሁን ዞር ብሎ ሊያያቸው አለመቻሉን ምንጮቹ ተናግረዋል።


ማዳበሪያው እየተጫነ ያለው ደግሞ ከገላን የባቡር ወደብ ሲሆን ስራው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው ደግሞ በኦሮሞ ተወላጆች ብቻ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በዚህ ደረጃ ማዳበሪያን እየዘረፈ ያለው አገዛዝ ነኝ የሚለው አካል ትላንት መሸንቲ ላይ ማዳበሪያ በጠየቁ አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ መክፈቱን ይናገራሉ።


የኦነጉ ሰራዊት ከባህርዳር በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው መሸንቲ ከተማ ላይ በከፈተው በዚህ ተኩስ በአርሶአደሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ምንጮቹ ይናገራሉ።


መሸንቲ ላይ የተጀመረውን ጥቃት ወደ መራዊ ለመውሰድ ጥረት ሲያደርግ የነበርው የኦህዴዱ ኦነግ ስብስብ ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ መካሄዱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ከዚህ ጋር ተያይዞ ትላንት በአካባቢው ዋና መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውንም ሳይተጠቁሙ አላለፉም።


የመራዊና አካባቢው ማህበረሰብም ይሄ ገዳይ ቡድን ወደ አካባቢው እንዳይገባ ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ መዋሉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ትላንት ተዘግተው የነበሩ መንገዶችን በኦህዴዱ የመከላከያ ሃይልና በብአዴኑ ካድሬዎች ለሊቱን ተከፍተው እንዲያድሩ ቢደረግም ማህበረሰቡ ግን አሁንም በተጠንቀቅ ሁኔታውን እየተከታተለ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page