በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ታክስ የማይክፈልበት በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እየተመዘበረ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በተለይ በየክፍለ ከተሞች አዳዲስ ሹመት በመስጠት ስም የሚወጣው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ያስቀምጣሉ።
ለሌብነት እንዲያመቻቸው በአንድ ክፍለ ከተማ በትንሹ አራት የቢሮ ሃላፊ እንዲመደብ ይደርጋል ይላሉ።
ለነዚህ የቢሮ ሃላፊዎች በመደበኛነት የሚከፈለው ገንዘብ እንዳለ ሆኖ ለእያንዳንዱ ታክስ የማይከፈለበት 16ሺ ብር እንዲመደብላቸው እንደሚደረግም ይናገራሉ።
16ሺ ብሩ ከታክስ ውጪ በሚል ሲመደብላቸው ምክንያት ተደርጎ የሚቀመጠው ደግሞ ለቤት ኪራይ የሚል መሆኑንም ያነሳሉ።
ለአራት ቢሮ ሃላፊዎች በአንድ ጊዜ 64ሺ ብር ወጪ እንደሚደረግ የሚያነሱት ምንጮቹ ይሄ ደግሞ በየክፍለከተማ ባሉት አመራሮች ልክ ሲታሰብ ደግሞ በሚሊየን የሚቆጠር ብር ከየክፍለ ከተማው በጀት መሰረቁን ያሳያል ይላሉ።
ለአራት ቢሮ ሃላፊዎች ይባል እንጂ በየጊዜው በየቦታው የሚሾመው አመራር ከፍተኛ ስለሆነ የገንዘቡም መጠን በዛው ልክ ይጨምራል ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።