top of page

(ኢትዮ 360 -ግንቦት 1/2015) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት በኦህዴዱ ወታደራዊ ሃይል ተከበበ።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነትና አካባቢው በኦህዴዱ ወታደራዊ ሃይል እየተከበበ መሆኑን የኢትዮ 360 አይን እማኞች ገለጹ።


አምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የፓትሪያርኩ ማረፊያን ጨምሮ የጳጳሳቱ መኖርያ የሆነው አካባቢ በከፍተኛ የኦህዴድ ሃይል በመከበብ ላይ መሆኑን ይናገራሉ።


በተለይም ዛሬ ከከሰአት በኋላ ጀምሮ በወታደራዊ ፓትሮል ተጭኖ የሚመጣና ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የኦህዴድ ሃይል አጠገቡ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ግቢ ውስጥ እንዲከማች መደረጉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ህገወጥ ሲኖዶስ አቋቁመናል ሲሉ የነበሩት እነ ሳውሪዎስ የእርቅ ጭምብላቸውን አውልቀው ሲኖዶሱን መረበሽ መጀመራቸውን ኢትዮ 360 በመረጃው ማውጣቱን ያነሳሉ።


ከዛም አልፎ ደግሞ ህወሃትና የኦህዴዱ ኦነግ በጋር ቤተክርስቲያኗን ለማፍረስ መዘጋጀታቸውንም አስታውቋል።


እነ ሽመልስ አብዲሳም የግንቦቱን የሲኖዶስ ጉባኤ ለመበጥበጥና ሲኖዶሱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውንም ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ ባወጣው መረጃ ይፋ ማድረጉን ያነሳሉ።


እናም አሁን ነባሩን ሲኖዶስ አፍርሶ በኦህዴዱ ሲኖዶስ ለመተካት የተዘጋጀው የነሽመልስ ቡድን ሰራዊቱን ልኮ አባቶችንና ቤተክህነቱን እያስከበበ መሆኑን ጠቁመዋል።


ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሃይልም ዛሬ ከሰአት በኋላ በብሔራዊ ሙዚየም ግቢ ውስጥ በወታደራዊ ፓትሮል ተጭኖ የሚመጣው ሃይል እየተራገፈ መሆኑን ነው የኢትዮ 360 የአይን እማኞች የተናገሩት።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page