top of page

(ኢትዮ 360-ግንቦት 2/2015) በአማራ ክልል በሽምግልና ስም በማዘናጋት አዲስ ዘመቻ ሊጀመር ነው።


በአማራ ክልል የጀመረው ዘመቻ ያልተሳካለት የኦህዴዱ ስብስብ በሽምግልና ስም በማዘናጋት አዲስ ዘመቻ ለመጀመር እቅድ መንደፉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


በሽምግልና ስም የሚላኩት ካድሬዎችም ዋና አላማ እርቅ ለማውረድ ሳይሆን የፋኖ ህዝባዊ ሃይሉ አመራሩም ሆነ አባሉ ያለውን አቋም ለማወቅና የያዘውንም ሃሳብ ይዞ ለመመለስ መሆኑን ያነገራሉ።


ሰራዊቱን አቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያ ልብሱ ላይ በመግጠም ጭምር ወደ ውስጥ ያስገባው የኦህዴዱ አገዛዝ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የሚያገኘው ግብአት በዋናነት አዲሱን ዘመቻ ተግባራዊ ለማድረግ እንደመሳሪያ የሚጠቀምበት መሆኑንም አንስተዋል።


በሽምግልና ስም በአማራ ህዝባዊ ሃይል ላይ የልየታ ስራ እሰራለሁ ብሎ ያሰበው የኦህዴዱና የብአዴኑ ካድሬ ስብስብ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውንና ከነመሳሪያው የተበተነውን የልዩ ሃይልም አድኖ ለመያዝ እቅድ መያዙንም ያስቀምጣሉ።


ህዝባዊ ሃይሉን በድሮን ጭምር ለመጨረስ እቅድ የያዘው አብይ አህመድ ለብአዴን አመራሮች ትእዛዝ በመስጠት ተግባራዊ ለማድረግ አሁንም እቅዱን ይዟል ብለዋል።


አዲስ እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለው ይሄው ገዳይ ቡድን የክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች ሳይቀር ምሽጎችን እየቆፈረ መሆኑንም ያነሳሉ።


ከጎንደር አዘዞ ወደ ሎዛ ማርያም መተማ መውጫ ሎዛ ማርያም ቀበሌ ገበሬ ማህበር አደርጅሀ ከምትባል ገጠራማ መንደር ኬላውን የጣለው የኦህዴዱ ሃይል የአካባቢውን አርሶ አደር በማማረር ላይ መሆኑንም ይናገራሉ።


በአካባቢው ባሉ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በማባረር ጭምር ምሽጉን የሰራው ይሄው ስብስብ አርሶ አደሩን ምግብ አምጣ ብቻ ሳይሆን ሴት ልጆቹንም እየደፈረበት ነው ሲሉ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ አመልክተዋል።


በተለይ የኦህዴዱ ሃይል በደረሱ ሴት ህጻናት ላይ እየፈጸመ ያለው አስገድዶ መድፈር ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብትን የሚገፉ አጸያፊ ስድቦችም የህብረተሰቡ ብሶት እንዲጨምር አድርጎታል ባይ ናቸው።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለስርአቱ ስጋት ናቸው፣ፋኖን ይደግፋሉ የተባሉና አሁን ለሚጀምረው ዘመቻም እንቅፋት ይሆናሉ የሚባሉ ወጣቶች በጅምላ እየታፈሱ መሆኑን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የተናገሩት።


በተከታታይ ደብረብርሃን ከተማ ላይ ወጣቶችን ሲያፍን የከረመው ስብስብ በወሎ፣በጎንደር፣በጎጃምና በሸዋ የተለያዩ አካባቢዎችም የእስር ዘመቻውን ቀጥሎበታል ብለዋል።


ይሄንን አፈናና ማሳደድ በዋናነት እያስፈጸመ ያለው ደግሞ በየወረዳውና ቀበሌው የተቀመጠው የብአዴኑ ሆድ አደር ካድሬ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comentários


bottom of page