በአዲስ አበባ ለሚ ኮራ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው የክብር ደመና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአዳነች አበቤ ትእዛዝ ሰጪነት የአማራ ቤቶች እንዲፈርሱ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮ 360 ምንጮች ስታወቁ።
አዳነች አበቤ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ስትመጣ በለሚ ኩራ ወረዳ 2 የክብር ደመና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለኦሮሞ አርሶ አደሮች መሬት ማደሏን ይናገራሉ።
እነዚህ አርሶ አደሮች ደግሞ የተሰጣቸውን መሬት ለአማራ ተወላጅ ወገኖቻቸው ይሸጡና የአማራ ተወላጆቹም በአካባቢው ቤት መገንባታቸውን አመልክተዋል።
ነገር ግን ሰሞኑን አዳነች አበቤ አርሶ አደሮቹ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠሩ በማድረግ ዛቻና ማስፈራሪያ ስትሰጥ መዋሏን ገልጸዋል።
እንደ አዳነች አባባል ከሆን መሬቱ ለኦሮሞ አርሶ አደር የታደለው አላማ ስላላቸውና እየሰሩት ላለው አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የመሰልቀጥ እቅድ ማሳኪያ መሆኑን በሚገባቸው ቋንቋ መናገሯን ያነሳሉ።
በተለምዶ የክብር ደመና በሚል የሚጠራው አካባቢ በአማራ ተወላጆች መያዙ ያናደዳት አዳነች በቀጣዩ ቀን ከከተማው የቤቶች አስተዳደር የተመደበ አመራርን ልካ ቤቶቹ በተሰሩበት አቅጣጫ ልኬት እንዲካሄድና መንገድ ይሰራበታል በሚል ቤቶቹ በአስቸኳይ እንዲፈርሱ ቀጥታ ትእዛዝ ማስተላለፉን ነው የሚናገሩት።
የክብር ደመና ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ለሃያት የጋራ መኖሪያ ቤት ቅርብ እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮች ይሄ ደግሞ እንደ አዳነች አበቤ በስመ ሸገር ስም ሲያፈርሱት የነበረውን ቤት ጨርሰው ወደ ከተማው የመሸጋገራቸው ማሳያ ነው ይላሉ።
ፒያሳን ጨምሮ በአፍንጮ በርና በተለያዩ የከተማዋ አይን በሚባሉ አካባቢዎች የነበሩ መኖሪያ ቤቶች በዚሁ ወንጀለኛ ቡድን እየፈረሱ መሆኑን ኢትዮ 360 በመረጃው በተከታታይ ማውጣቱ ይታወሳል።
አሁንም በዚሁ የአማራና የሌሎች ብሔር ተወላጆችን ቤት እየመረጡ የማፍረሱ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
አሁን ላይ በሁሉም ነገር ሊሳካለት ያልቻለውና በፖለቲካው ቁማሩን የተበላው የኦህዴዱ ብልጽግና ትኩረቱን ሁሉ ሃብት ማካበትና ዝርፊያ ላይ ራሱን አሰማርቷል ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።
Comments