ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከህብረተሰቡ የተዋጣውን ገንዘብ ለቤተመንግስት ግንባታ በሚል ሊወሰድ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።
ለ12 አመት ያህል ለህዳሴ ግድብ በሚል ከህብረተሰቡና በውጭ ካለው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ገንዘብ ሲዋጣ መቆየቱን ያነሳሉ።
አሁን ላይ ታዲያ በዋና ሌብነት ላይ የተሰማራው የብልጽግናው ስርአት ይሄን ገንዘብ ለቤተመንግስት ግንባታ በሚል ለመውሰድ ዝግጅቱን ጨርሷል ባይ ናቸው።
ለዚህ ሌብነት እንዲያግዝ ደግሞ ይሄ የግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ ያለምንም የደሞዝ ጭማሪ ሲሰሩ የነበሩ ባለሙያዎችና ሰራተኞችን ለማባረርም እቅድ ተያዟል ብለዋል።
ይሄንን እቅዳቸውን ለማሳካትም በተለያየ መንገድ ሰራተኛውን ማማረርና ከዚህም ጋር ተያይዞ ስራውን እንዲለቅ እየተደረገ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በተደጋጋሚ ኢትዮ 360 በመረጃው ከህዳሴው ግድብ ግንባታና ከሰራተኛው ጋር በተያያዘ የኦህዴዱ ስርአት የሰራቸውንና እየሰራቸው ያሉ ወንጀሎችን ሲያጋልጥ መቆየቱ ይታወሳል።
አሁን የህዳሴው ግድብን ገንዘብ በመመዝበርና ሰራተኛውን ከስራ ገበታ ለማባረር የተያዘው እቅድም የዚሁ ወንጀል አንዱ አካል መሆኑን ምንጮቹ ያስቀምጣሉ።
Comments